ክፍል ሰባት
ምዕራፍ አራት
ለአቅመ ሔዋን የመድረስ
ምልክት
ፈጣን
የቁመት ማደግና የክብደት መጨመር ከመከሰቱም ሌላ የሽንጥ መርዘም፣ የደረት መጋጠሚያ መጎድጎድ፡፡ በአንዳንድ ሴቶች ላይ ደግሞ ብጉር
በሰውነታቸው በተለይ በፊታቸው ላይ በዝቶ የሚታይ ሲሆን የፊት ቅርጽም ቀስ በቀስ እየተለወጠ ይሄዳል፡፡ በብብትና የብሽሽት (ኀፍረተ
አካል) አካባቢ ጸጉር መብቀል ጋር ዳሌዎች ይሰፋሉ፡፡ ልጃ ገረዶች የሚኖራቸው ሰፋ ያለ ዳሌ ወሊድን ብቻ ሳይሆን ከወለዱ በኋላ
ሕጻናትን ለማዘልና ለማቀፍ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል፡፡ የጡት መጎጥጎጥ ለአቅመ ሔዋን የመድረስ ጉልህ ምልክት ነው፡፡ አንዲት
ኮረዳ የሚኖሩአት ሁለት ጡቶች ልጅ በምትወልድበት ጊዜ ለሕጻኑ ምግብ የሚሆነውን ወተት ማመንጨት ይጀምራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
‹‹ጡቷ ሁልጊዜ ታርካህ፣ በፍቅርዋም ሁል ጊዜ ጥገብ›› (ምሳ. 5፡19) ማለቱ ባልዋ የሚደሰተው ጡቶቿን በመሳም፣ በመነካካትና፣
በመዳባበስ ነውና፡፡ ለጡት ማነስ እና መተለቅ የሚያሳስብ አይደለም፡፡ የተፈጠረበትን ዓላማ ስለማያጓድል ሊጨንቀን አይገባም፡፡ በጡት
መያዣ የሚወጥሩ፣ ምናምን የሚወትፉ፣ ቀዶ ጥገና የሚያስደርጉ ሴቶች አሉና፡፡ ነገር ግን ሠለስቱ ምዕት ‹‹ሌላ መልክ አትሻ(መነቀስ፣
መጠቆር፣ መታከም) በተፈጥሮ ያገኘኸው ይበቃሃልና›› ብለው አስተምረዋል፡፡
ጡት
በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል ስለሆነ ከመጨነቃችን የተነሳ የማናውቃቸውን ነገሮች እንደመሰለን መጠቀም ጉዳት ላይ ሊጥለን ይችላል፡፡ ለጡት
ካንሰር መጋለጥ...፣ አንዳንድ ሴቶች ደግሞ በጡታቸው ምክንያት የሰውነት ቅርጻቸው የተበላሸ መስሎአቸው የሚጨነቁ፣ የዐይን ዝሙት
በያዛቸው ወንዶች ዘንድ ቦታ ያጡ ስለመሰላቸው ይጨነቃሉ፡፡ ውጫዊ አካል የሚመለከት ወንድ እውነተኛ ፍቅር በውስጡ የለም ያ አካል
ሲያልፍ እሱም አብሮ ያልፋል፡፡ ባሁኑ ጊዜ ለውጫዊ አካል የሚጨነቁ ሴቶች የበዙበት ምክንያት ውጫዊ አካል ላይ ያተኮሩ ወንዶች ስለበዙ
ነው፡፡ ነገር ግን ከቅርጽና ከውበት ይልቅ ጤንነት ይበልጣል፡፡ ሴቶች በሚወልዱበት ጊዜ ልጆቸቻቸውን እያጠቡ የማሳደግ ኃላፊነት
አለባቸው፡፡ ጡትን የሚተካ ምግብ የለምና፡፡በፍት.ነገ. ‹‹ልጆቿን ለሞግዚት አትስጥ›› ይላል፡፡ምክንያቱም አንዳንድ ሴቶች መውለድን
እንጂ ሕጻናትን ማሳደግ አይፈልጉም- መከራን በመሰቀቅ፣ ዝሙትን በመውደድ እና እንዲሁም እግዚአብሔር የሰጠውን ምግብ መከልከል ስለሆነ
ግፍ ነው፡፡
የወር አባበ
ለአቅመ
ሔዋን የደረሱ ሴቶች የሚያሳዩት ሌላው ምልክት የወር አበባ ነው፡፡ የወር አበባ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ (ሀ) የሴቶች ልማድ
ዘፍ. 18፡11 ልማደ አንስት (ለ) በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ዘፍ. 31፡35 (ሐ) የወር አበባ የተባለበት ምክንያት በየወሩ የሚታይ
ስለሆነ አበባ መባሉ ፍሬ ለመስጠት የሚችል እንቡጥ (አበባ) ስለሆነ ነው፡፡ (መ) አደፍ ተብሏል (ሠ) ደመ ጽጌ ይባላል ‹‹የአበባ
ደም›› ማለት ነው፡፡ የወንድ ዘር ባለማግኘቱ በደም መልክ ይወጣል፡፡ እስከሚጸንሱት በየወሩ ይታያል፡፡ በእርግዝና ወቅት ይቋረጥና
ልጅ ከተወለደ(ች) በኋላ ጤናማ ሂደቱን ይቀጥላል፡፡ ይህ ወርኃዊ ዑደት የሚጀምርበት፣ የሚቋረጥበት ዕድሜና መታየት ከጀመረበት እስከሚቋረጥበት
ድረስ የሚወስደው ጊዜ ከሰው ወደ ሰው ይለያያል፡
የወር
አበባ ሴት ልጅ ፈጣሪ ለመደበላት ዕጥፍ የሕይወት ሚና ማለትም ሚስት እናት ለመሆን መድረሷን የሚያመለክት በመሆኑ ሳትከፋ በጸጋ
ልትቀበለው ይገባታል፡፡ መደንገጥ፣ መፍራት አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ሲታያቸው የሚበሳጩ፣ በመታየቱም
የሚከፉ፣ ባይታይ ደስ የሚላቸው አሉ ነገር ግን ይህ በደል ነው፡፡ ወደ ትዳር ከገቡ በኋላ ባይታይ ግን ልጅ መውለድ የለምና ምን
ያህል ያስከፋ ይሆን? ስለዚህ እናቶች ለልጆቻቸው አስቀድመው በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥ አለባቸው፡፡ ልጆችም ለቤተሰቦቻቸው በግልጽ ማማከር
ይገባቸዋል፡፡ ዘፍ. 31፡35 ራሔል ‹‹በሴቶች የሚደርስ ግደዳጅ ደርሶብኛል›› ብላ ለአባቷ እንደ ነገረችው፡፡
V ድንግል ማርያም ግን
ለ64 ዓመታት ስትኖር ልማደ አንስት አላገኛትም፡፡ ሌሎችም ሳያዩ የሚያልፉ ጤናማ ሴቶች የሉም፡፡ ምክንያቱም እሷ ልዩ ናት ከአዳም
እና ከሔዋን የውርስ ኃጢአት ነጻ ስለሆነች ይህ አይመለከታትም፡፡
የወር አበባ መቼቱ
አዳምና ሔዋን በኃጢአት ከወደቁ በኋላ ከገነት ውጭ ነው፡፡ በገነት በነበሩበት ጊዜ ምንም እንኳን በሔዋን ባሕርይ ደመ ጽጌ የነበረ
ቢሆንም ደሟ በአፍአ አይታይም ነበር፡፡ በምድር ላይ ያለው ዝናብም በፊት እንዳልነበረ እና ከጥፋት ውኃ በኋላ ግን እግዚአብሔር
ክረምትና በጋን ለማፈራረቅ ለኖኅ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት ዝናብ መዝነብ ጀመረ (ዘፍ. 8፡22)፡፡ በፊት ውስጥ ለውስጥ ያረካት
የነበረው ውኃ ዝናብ ሆኖ እየመጣ ምድርን ከውጭ ያጨቀያት ጀመር፡፡ ምድር ለሔዋን ምሳሌ ናት ሰው ምድር ይባላልና፡፡ ዝናብ የወር
አበባ ምሳሌ ነው፡፡
በወር አበባ ወቅት
የሚያጋጥሙ የሕመም ስሜቶች አሉ፡፡ የጡንቻና የአጥንት መልፈስፈስ (ድካም)፣ የወገብ ሕመም፣ የሆድ ቁርጠት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣
ትዝብት ላይ እስከ መውደቅ የሚያደርስ መቅበጥበጥ አንዳንዴም የመደበር፣ በሆነው ባልሆነው በቀላሉ የመከፋት ስሜት ይነበባል፡፡ ዘፍ.
31፡35 ያንብቡ፡፡
የወር አበባ ርኩስ ነውን?
በብሉይ ኪዳን እርግጥ
ነው ይባላል፡፡ ዘሌ. 18፡19፣ ዘሌ. 20፡18 እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡... ‹‹በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች››...‹‹ባለ
መርገም ሴት››... ‹‹ከርኩሰትዋ ነጽታ››
በሐዲስ ኪዳን ግን
ማለት አይቻልም፡፡ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ ክህደት ነው ምክንያም ጌታችን አምላካችን በመስቀል ላይ ዋጋ ስለከፈለልን መርገም አይባልም፤ሆኖም
ግን የወር አበባ ርኩሰት ባይሆንም አደፍ (አዳሪ) ነው ማለትና ርኩሰት ነው ማለት መካከል ከፍተኛ ልዩነት አላቸው፡፡ ርኩሰት ውስጣዊ
ነው፡፡ በንስሐ እንጂ በውኃ አይጠራም፡፡ አደፍ ግን አፍአዊና በግዘፍ የሚታይ ነው፤ውኃ ያጠረዋል፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህርይ
ሳለ እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም ሰውነት ሲያስወግደው ግን እንደ ቆሻሻ ይቆጠራል፡፡ ለምሣሌ፡- ዛሕል (ንፍጥ)፣ ሽንት፣ ምራቅ፣ ዓይነ
ምድር (እዳሪ)፣ ላብ በሰው ባሕርይ በሰውነት ውስጥ ሳሉ ጠቃሚና አስፈላጊ ነበሩ፡፡ሲያስወግዳቸው ግን እንደ ጉድፍ ይቆጠራሉ፡፡
ግን ርኩሰት አይባሉም፡፡ የወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡
በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው
1.
ከሩካቤ፡- በሽታ ያስከትላል፣
የወንድ ዘር ክቡር ስለሆነ፣ ‹‹እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኀፍረተ ስጋዋን ትገልጽ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ›› (ዘሌ.
18፡19)ይላልና፡፡ በዘሌ. 20፡18 ‹‹ማንኛውም ሰው ከባለመርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ እርሷም የደሟን ፈሳሽ
ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ፡፡›› በሐዲስ ኪዳንም እንደ ብሉይ ኪዳን በድንጋይ ተወግረውና በእሳት ተቃጥለው
እንዲጠፉ ባይደረግም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመተላለፋቸው በመንፈሳዊ ቅጣት(በቀኖና) መቃጣቸው አይቀርም፡፡
2.
ከመጠመቅ፡ 1ጴጥ. 3፡21
‹‹ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት... የሰውነት እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፡፡››
ስለዚህ ከጥምቀት በፊት የሰውነት አደፍ ማሰወገድ ያስፈልጋል፡፡ የወር አበባ አደፍ ስለሆነ መጠመቅ አይቻልም፡፡ ፍትሐ.ነገሥ.
‹‹በምትጠመቀው ሴት በምትጠመቅበት ቀን አደፍ ቢመጣባት እስክትነጻ ድረስ ትቆይ›› አንዳንድ ጊዜ በጠና የታመሙ ሰዎች በጸበል ለመፈወስ
ክትትል ሲጀምሩ ልዩ ልዩ ፈተና ያጋጥማቸዋል፡፡ የወር አበባ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያለማቋረጥ ወይም በተደጋጋሚ መከሠቱ ነው፡፡
በዚህን ጊዜ ከሰይጣን ጋር እልሕ መጋባትና ዝም ብዬ ብጠመቅ ምን አለበት? ማለት ሞኝነት ነው፡፡ ‹‹ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ
በክፉ አትሸነፍ›› (ሮሜ. 17፡21) ይላልና ‹‹ይህ ዓይነት ከጸሎትና ከደም በቀር አይወጣም›› (ማቴ. 17፡21) መርሳት ይሆናል፡፡
በዚያን ጊዜ በተለየ መልኩ መጾም እና መጸለይ ያስፈልጋል፡፡
3.
ከመቁረብ፡- ለቁርባን የሚያሰፈልገውን
ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ ቢሆኑም ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ መቀበል አይችሉም፡፡ በወር አበባ ላይ እያለች እንድትቆርብ ያደረገ ካህን፣
ዲያቆን፣ ከክህነቱ ይሻር፡፡ ፍት.ነገ. 6 ዘሌ. 7፡19-21፡፡ ስጋወደሙን መቀበል ቢኖርብንም በምንም አመካኝነት ቢሆን በወር
አበባ ላይ ሳለን መቁረብ አንችልም፡፡ በቁርባን የሚጋቡ ሰዎች የሰርግ ቀናቸውን ከመወሰናቸውና የሰርግ ዝግጅት ከመጀመራቸው በፊት
የሴቷን የወር አበባ ዑደት ለይቶ ማወቅና ከሠርግ ቀኗ ጋር አንድ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንዲሁም የጋብቻ ቀናቸውንም በአባቶች ጸሎት
መወሰን እንጂ በዓለማዊ ዝግጅቶች መወሰን የለባቸውም፡፡ መጸለይ መፍትሔ ነው (የሰይጣን አሰራር እንዳያዛባ)፡፡
4.
ቤተ መቅደስ ከመግባት፡-
ከግዳጅዋ ከነጻች ከሰባት ቀን በኋላ ገላዋን ታጥባ ትገባለች፡፡ ፍት.ነገ. አን. 6፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን አትሂድ
ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያውን ቅጽር ከገባች በኋላ መጠለያና በገራገር ውስጥ ሆና ትጸልይ፣ ትማር፣ ማንኛውንም መንፈሳዊ
ነገር ትከታተል እንጂ ወደ ቤተ መቅደስ ተደፋፍራ አትግባ ማለት ነው፡፡
ወደ ቤተ መቅደስ የማይገባበት ምክንያት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይማሩ
No comments:
Post a Comment