ክፍል አስር
.... የቀጠለ....ስለ
ድንግልና
ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅም
1.
በአግባብ ለመኖር፡-
በድንግልና መኖር አግባብ ነው ዝሙት ግን ግብረ ገብነትን ማጣት ነው፡፡ ድንግልናን ጠብቆ ለመኖር የሚደረገው ትግል
ሕጋዊ ሰው ሆኖ መኖርን ያለማምዳል፡፡
2.
ሳይባክኑ ለመኖር፡-
ድንግልናውን የጠበቀ ወዲህና ወዲያ አይልም፡፡ ዝሙት ግን መባከን ነው፡፡ ዝሙተኛ ኃጢአቱን ለመደበቅ፣ ከዚህ በኋላ
እግዞ,ዚአብሔር ምን ያመጣብኝ ይሆን? በማለትና ዝሙቱ ቢታወቅ በሌሎች ዘንድ ምን ሊባል እንደሚችል በማሰብ በስጋትና በመባከን ይኖራል፡፡
መዝ. 6፡1-3፣ 1ቆሮ. 7፡32-33፡፡ በጋብቻ ከመኖር በድንግልና መኖር የበለጠ ከሐሳብ ነጻ ያደርጋል፡፡ ወጣቶችም በዚህ ሕይወት
ለመኖር ከወዲሁ ከእግዚአብሔር ጋር ብነጋገሩ እና ቢወስኑ እጅግ በሕይወታቸው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
3.
በጌታ ይጸናል፡- ብዙዎች ስለ ፍትወት
ብለው ኮረዳና ጎልማሳ ፍለጋ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን አንደተው የሚታወቅ ነው፡፡ ዛሬም የመናፍቃን ትልቁ አጀንዳ የሆነው ሴቶች ረጋፊ
የሆነ መልካቸውን ተጠቅመው ኦርቶዶክስ ወጣቶችን የነጠቁ ብዙ ናቸው፤ ወንዶችም እንዲሁ እህቶቻችንን፡፡ ለመሆኑ የጋብቻ የመጀመሪያ
መስፍርት እኮ ሃይማኖት ነው፡፡ ከዚያ የተረፈ ገንዘብ፣ መልክ፣ ጎሳ፣ ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋ፣ የመሳሰሉት የጋብቻ መስፈርት ሊሆኑ
አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር እና ቅዱሳኑ በእነዚህ መስፈርቶች ውስጥ የሉምና፡፡ ለመሆኑ ላንተ (ላንቺ) የተዳር መስፈርትሽ ምንድነው?
ባሁኑ ጊዜ የተዳር መስፈርቱ ውጫዊ ነገር ስለሆነ የጋብቻ ክብር ቀንሷል፡፡ ጋብቻ እኮ የመጀመሪያ ተቋም ነው በዚህ ዓለም ላይ ያለው
ሕዝብ ሁሉ የተገኘበት፣ በገነት ውስጥ በእግዚብሔር የተመሠረተ፡፡ 2ጴጥ.2፡1-2፣ 1ቆሮ. 7፡37፡፡ ድንግልናን መጠበቅ ራሱ ትዕግስት
እና ጽናት ስለሚጠይቅ ይህን ይለማመዳሉና በእግዚአብሔር ለመጽናት ይረዳል፡፡
4.
ድንግልናን መጠበቅ
ታማኝነትን ያረጋግጣል፡- ድንግልናን ጠብቀን እንድንይዘው በአደራ የተሰጠን የከበረ ንብረት ነው፡፡ ባለአደራ
ፈጣሪያችን፣ በሚያስፈልግ ጊዜና ሰዓት ለትዳር አጋራችን እንድንሰጠው ይጠብቀናል፡፡ ድንግልናውን ያልጠበቀ ግን አደራ በሊታ፣ ታማኝነትም
የጎደለው ይሆናል፡፡ ድንግልና ሳይኖራቸው የተጋቡ ሰዎች ሳይተማመኑ ይኖራሉ፤ ይህ ደግሞ ለአንድ ትዳር ትልቁ ፈተና ነው፡፡ ምክንያቱም
ባልና ሚስት ተማምነው እና ተዋደው ይኖራሉ እንጂ ተቻችለው አይደለም፡፡ የአንድ ሰው አካል ላይ ያሉ ብልቶች ተግባብተው፣ ተዋደው፣
አንድ ሆነው፣ ተማምነው ይኖራሉ እንጂ ግድ ተቻችለው አይደለም፡፡ ባልና ሚስትም እንዲህ ናቸው፡፡ ሚስት ለባሏ እግዚአብሔር በአደራ
የሰጣትን ድንግልና ስትሰጠው በአደራ ጠባቂነት እንዲያያት፣ እንዲያምናት፣ እንዲያከብራት፣ እንዲወዳት ያደርገዋል፡፡ ያን ጊዜ ይዋደዳሉ፣
ይከባበራሉ፡፡ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰው ግን እንደ ተራ ነገር ይቆጥራል፡፡ ድንግልናን መጠበቅ ችሎታ ነው፡፡ ምክንያቱም
በውስጡ ጽናት፣ ብርታት፣ ትዕግሥት፣ ታማኝነት አለበትና፡፡
5.
ድንግልናን መጠበቅ
መጠንቀቅ ነው፡- ከበሽታ፣ ያለ አግባብ ወይም ሳያገቡ ከመውለድ፣ ክብርና መልካም ስምን ከማጣት፣ ከመጸጸት ያድናል፡፡ ለወደፊት መንፈሳዊውም
ሆነ ሥጋዊ ችግር ከሚፈጥሩ የኑሮ ጠንቆች ሁሉ መቶ በመቶ ሊሰወር የሚችል መጠንቀቅ ቢኖር ድንግልናን መጠበቅ ነው፡፡
6.
ልብ ሳይከፈል ፈጣሪን
እጅግ አድርጎ ለማስደሰት፡- ባሏንም ታስደስታለች(ከዚህ ይጀምራልና)፡፡ ድንግልናን ካጠፉ በኋላ የሚደረግ ጋብቻ
አግብቶ የፈታ ሰው እንደሚፈጽመው እንደ ሁለተኛ ጋብቻ ይቆጠራል፡፡ስሙም የመዐስባን ጋብቻ መባሉ ለዚህ ነው፡፡ ለመመንኮስ ተስሎ
የነበረ ሰው ቢያገባ የተሳለው ስእለት እንደ መጀመሪያ ጋብቻ ተቆጥሮ የሚፈጽመው ጋብቻ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያገባ ሰው እንደሚቆጠርበት
ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ያስረዳል፡፡ በ1ቆሮ. 7፡33-34 ‹‹የተጋባች ግን ባሏን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለም ነገር ታስባለች፡፡››
ድንግልናቸውን አጥተው የተጋቡ ባለትዳሮች ያጡበትን መንገድ በሕሊናቸው ማሰባቸው አይቀርም፡፡ ያንጊዜ ደግሞ ላሉበት ትዳር ደስተኛ
አይሆኑም፡፡ ምንም እንኳን በአካል መዋሐድ ቢችሉም የልቡና ተዋሕዶ ለመፍጠር ይቸገራሉና ደስታቸው በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ እንደዚህ
ዓይነት ትዳር የሚመሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ ሰማያዊውን ዋጋ ትተው የዚህን ዓለም ቢዝነስ፣ ኑሮ፣ደስታ ወዘተ ሲያወሩ፣ ሲያስቡ እና ስያደርጉ
ይኖራሉ፡፡ የትዳር መስፈርታቸውም ከእነዚህ የራቀ አይደለም፡፡
7.
ድንግልናን መጠበቅ
ጋብቻ ሳይዘገይ በጊዜው እንዲፈጸም ይገፋፋል፡- ከጋብቻ በፊት ዝሙት ከተፈጸመ ለጋብቻ ያለው ውስጣዊ ፍላጎት ይቀንሳል፤
እንደመታሰርም ይቆጥሩታል፡፡ ባሁኑ ጊዜ የሚታዩ እውነታዎችም ይህን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ብዙ ዓለማዊ ፊልሞችም ከጋብቻ በፊት ዝሙትን
የሚያበረታቱ ስለሆኑ ወጣቱ ሊርቃቸው ይገባል፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሩካቤ የጋብቻ ቀነ ቀጠሮ እንዲራዘም ከማድረጉም በላይ ለመለያየትም
በር ከፋች ነው፡፡ ቢጋቡ እንኳን የውጪው ሰው ምን ይለናል በማለት እንጂ ፈልገውት አይደለም፡፡ ከላይ እንዳልኳችሁ ዝሙት እንደፈጸሙ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይለያቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ፍቅራቸው ይቀንሳል መበሳጨት፣ መጨቃጨቅ፣ መነዛነዝ ይጀምራሉ፤ ይህ ጭቅጭቅም
በትዳራቸው ውስጥም ይቀጥላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሰዋልና አንድነት የላቸውም፡፡
የአንድን ሰው ድንግልና ሊያሳጡ የሚችሉ ወቅቶች፣ ቦታዎችን እና አጋጠሚዎች
ከሰንበት ትምህርት ቤት ጓደኞቻችሁ፣ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ተመካከሩ፡፡ አደራ፡፡ እኔ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ እነሆ!
አንዳንዶች ገና በልጅነትና በመጀመሪያዎቹ የወጣትነት አፍላ ጊዜያት
ድንግልናቸውን ያጣሉ፡፡ ሌሎች አስቸጋሪውን የወጣትነት ዕድሜ አጋምሰው ክብራቸውን የሚያጡበት ሁኔታ ይፈጠራሉ፡፡ ተገድደው ሊደፈሩ
ይችላሉ (ዘደ. 22፡24) ነገር ግን ሴቶች ራሳቸው ለመደፈር ሁኔታ ያመቻቹ መሆን የለባቸውም (አለባበሳቸው፣ ውሎአቸው መታየት
አለበት)፡፡ ከወንዶች ጋር ያለው አቀራረብ ገደብ ሊበጅለት ይገባል፡፡ሰውን በማመን የተጎዱ ብዙ እህቶች አሉና፤ ሰውን መማን አያጸድቅም
ማፍቀር (መውደድ) ነው እንጂ!
ግን አንድ ጥያቄ ላንሳ! ከጋብቻ በፊት ድንግልናቸውን ያጡበትን ቀን
በደስታ ነው ወይስ በሀዘን ነው የሚያስቡት?
No comments:
Post a Comment