ክፍል ሁለት
ምዕራፍ ሁለት
ወጣቶች እና ፈተናዎቻቸው
1. የወጣቶች ምኞት
በወጣትነት ዘመን አካላት እንደሚደራጁ እና አእምሮአቸው እንደሚዳብር ሁሉ ምኞታቸውም በዓይነት እና በመጠን እየሰፋ እና
እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ይህም በአመዛኙ ከመንፈሳዊነት ጋር የሚቃረን እና ሥጋዊ በመሆኑ ‹‹እኩይ ፍትወት›› ይባላል፡፡ 2ጢሞ. 2፡22
‹‹አንተ ግን ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ሽሽ በንጽሕናም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል፡፡››
እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ወጣትነት የሚሠሩበት ዘመን እንጂ የሚመኙበት ዘመን አይደለም፡፡ እኛም ወጣቶች ምኞታችንን ወደ ጎን በመተው የሥራ ሰዎች ልንሆን ያስፈልጋል፡፡ያለ ሥራ ምኞት የሚደረስበት አይደለም፡፡
ያዕ. 1፡13 ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም
ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብ እና ሲታለል ይፈተናል፡፡ ይህም ምኞት ወደ ጥፋት የሚስብ የሚጎትት እና የሚያታልል ነው፡፡
‹‹በገዛ ምኞት ሲሳብ›› ማለት ምኞት ከፍተኛ ጉልበት እንዳለው ይጠቁማል፡፡በወጣትነት ዘመን ምንም አእምሮ የበሰለ ቢሆን ከዚያ
የሚበረታው ግን ምኞት ነው፡፡ ከወጣቶች እውቀት ይልቅ ምኞታቸው መበርታቱን ለማስረዳት ወጣቶች በዘመነ ኦሪት ይመሰላሉ፡፡ ሕገ ልቡና
እንደመሰለው መኖር ሕግ ኦሪት የሰው ባሕርይ በኃጢአት የጎሰቆለ ስለነበር ሕጉን ፈጽመው ለመጽደቅ አልተቻለም ነበር፡፡ ወጣቶችም
እውቀታቸው እየጨመረ ቢመጣም ምኞታቸውም የዚያኑ ያህል ስለሚበረታና ስለሚስባቸው እውቀታቸውን ተጠቅመው የሚያጽደቃቸውን ጎዳና ለመከተል
ይቸገራሉ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ. 7፡23 ‹‹በብልቶቹ ውስጥ ያለው ይህ የኀጢአት ሕግ (ምኞት) ወደ እርሱ ማረከኝ ተበረታታብኝ››
ሊቁ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጎልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጎበኙሽ እንጂ››
ብሎ ወጣቶች በምኞታቸው ተሸንግለው ሌላውን ለማታለል እንደሚያባብሉ ይናገራል፡፡
ምኞት በውስጣችን እንዲኖር እና እንዲያድግብን የምንከባከበው ነገር መሆን የለበትም፡፡ ምኞት ተስፋ አይደለምና፡፡ ጠቢቡ
ሶሎሞን በምሳ. 21፡26 ‹‹ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፡፡›› ይላል፡፡ምኞት አስደሳች እና ጣፋጭ ነገር ትመስል ይሆናል ነገር
ግን አይደለችም፡፡ ‹‹ምኞት ስሕተት እና ውድቀት ናት እንጂ ጣፋጭ አይደለችም›› (ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡ ምኞትን ማብዛት ልፋትን
ወይም ተስፋ መቁረጥን ማብዛት ነው፡፡ምክንያቱም ምኞትን ለማሳካት ብዙ መድከም ከማስፈለጉም በላይ ብዙ ምኞት ካልተሳካ የሚያስከትለው
ተስፋ መቁረጥም እንደዚሁ ይሆናል፡፡ ብዙ ወጣቶች የሚመኙት ጉዳት የሚያስከትልባቸው እና ከጥቂት ጊዜ በኋላ በብርቱ የሚያስቀጣቸውን
ነገር ነው፡፡የሚገርመው ግን ጓጉተው የሚፈልጉት እንጂ ሲያገኙት ወዲያው የሚሰለቹት ወይም የሚጸጸቱበት ነው፡፡
ፈጣሪን ሳይጠጉ ምንም ነገር አርኪ እና በቂ መሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ መመኘት እና ለማግኘት ብቻ ሳይሆን አስቀድመን
ፈጣሪን መጠጋት ይኖርብናል፡፡ በወጣትነት የሚከሰት ምኞት አንድ ብቻ አይደለም፡፡ ወጣቶች ሁሉም ስለሚያምራቸው በአንድ መርጋት አይሆንላቸውም፡፡ተምሮ
በመአረግ መመረቅ፣ አጭቶ ማግባት፣ ሀብታም ነጋዴ መሆን፣ትልቅ ባለሥልጣን መሆን ተራ ጠብቀው ብታሰቡ የሚሳኩ ይሆናሉ ካልሆነ ግን
‹‹ሁለት የወደደ አንዱን ሳያገኝ ሄደ›› ይሆንብናል፡፡ ስለዚህ ወጣቶች አንድን ነገር መጀመር ሳይሆን በእርጋታ ሆኖ እስከ መጨረሻ
መፈጸም አለባቸው፡፡ ወጣቶች ምኞቶቻቸው ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ሁለት የማይጣጣሙ ነገሮችን የሚመኙበት ጊዜ አለ፡፡ ሙሽራ ሲያዩ
ማግባት እና መውለድን ይመኙና በዚያው ቀን ደግሞ ልቡናቸው በመንፈሳዊ ነገር ተነክቶ መመንኮስ እና መመነን የሚመኙበት ጊዜ አለ፡፡
ይህ ደግሞ በአንድ ሰው መፈጸም ስለማይቻል መታወክ ነው፡፡ ብንታገሥ ግን ከጊዜ ብዛት ራሱ ይርቃል፡፡ ማቴ. 7፡25 ‹‹ዝናብም
ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንንም ቤት ገፋው በዐለት ላይም ስለተመሠረተ አልወደቀም፡፡›› በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል፡-
v ቤት የወጣትነት ሕይወት ነው፡፡
v ነፋስ ነፈሰ ማለት የአጋንንት ፈተና በወጣቱ ላይ ተነሳበት እና ከሴት ርቆ ንጽሕናውን ጠብቆ እንደ እንጦንስ እና እንደ
መቃርስ ለመኖር እንዲመኝ አደረገው ማለት ነው፡፡
v ዝናብም ወረደ ማለት ያንኑ ወጣት እንደ እንጦንስ እና መቃርስ መኖር አይቻለኝም ባይሆን እንደ ኢዮብ እና አብርሐም አግብቼ
ልጆች ወልጄ በሕግ ሊኑር አሰኘው ማለት ነው፡፡
v ጎርፍም ጎረፈ ማለት በመጨረሻ ተስፋ በመቁረጥ ሁሉንም አልችልም እስኪል ድረስ አደረሰው ማለት ነው፡፡
ዐለት የተባለው ግን
የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ወጣቶች ከፈቀዱ በእግዚአብሔር ቃል ላይ መመስረት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሕጉ ከውስጣቸው እንዳይጠፋ
ማድረግ ይችላሉ፡፡ 1ዮሐ. 2፡14 ‹‹የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ስለሚኖር...›› ፡፡
በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ
አስትምህሮ መሠረት ምእመናን በአምስት መደብ ይመደባሉ፡፡ ይህም መደብ ‹‹ጾታ ምእመናን›› ይባላል፡፡ እነዚህም
1.
ካህናት
2.
መነኮሳት
3.
አዕሩግ (አረጋዊያን)
4.
ወራዙት (ወንድ ወጣቶች)
5.
አንስት ወጣቶች
እነዚህ አምስቱ የጾታ
መደቦች በዐብይ ፈተና ይፈተናሉ፡፡
የካህናት ፈተናቸው
ትዝኅርት (ትዕቢት)
የመነኮሳት ስስት
የአረጋዊያን ፍቅረ
ንዋይ
የወጣቶች ዝሙት
የወጣት ሴት ፈተና
ደግሞ ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥ) ዮሐ. 5፡4 (ትርጓሜ) ይህ ማለት ግን ዋና ዋና ፈተናቸውን አንጓሎ መናገር ነው እንጂ እያንዳንዱ
ጾታ ምእመን የሚፈተነው በአንድ ነገር ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ በር የሚከፍቱ እና ለምእመኑ ረቂቅ እና ከባድ ስለሆኑ
ነው፡፡ ለምሳሌ ካህኑ ሰማያዊ ስልጣን ስላለው ሲተብት ትዕቢተኛ መሆኑን ለራሱ አያውቅም ሌሎችም እንዲሁ አያስተውሉትም፡፡ ሰውነቱ
በደዌ የተጠቃ ሰው ጉንፋን እንኳን አንደሚያይልበት እንዲሁ በዋና ፈተናው ድል የተደረገ ምእመን ሌሎች ጥቃቅን ፈተናዎች ይረባረቡበታል፡፡
ነገር ግን ዋናውን ፈተና ድል ካደረገ የሚመጡበትን ሌሎች ፈተናዎች በቀላሉ ድል ለማድረግ ይቻለዋል፡፡ ወጣቶች እድሜያቸው እየገፋ
በመጣ ቁጥር ወጣትነታቸው ሲያልፍ የወጣትነት ፈተናቸውም አብሮ እንደሚያልፍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈቀርቅ ‹‹በወጣትነት ወራት ደዌ ኀጢአት
ትያዛለች... ከእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋ ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል››ይላል፡፡
2. የወጣትነት ምልክቶች
ብዙ የአካል ለውጥ
ይታያል፡፡ ቀጭን ድምጽ (ሴት)፣ ጎርናና ድምጽ (ወንድ)፣ የአዳም ፍሬ የሚባለው ማንቁርት ማደግ፣ ብጉር፣ በተለያዩ አካላት ፀጉር
ማብቀል፣ ከራስ እስከ ጽሕም በግራ እና በቀኝ የሚወርድ ለጊዜው ለስለስ
ያለ እና ስስ ጠጉር ወይም ሪዝ ማቆጥቆጥ ይጀምራል፡፡ ይህን ፂሕም መከርከም እና መቀነስ እንጂ ሴት እስኪመስሉ ድረስ ሙሉ በሙሉ
ንጭት አድርጎ ማንሳት የሚገባ አይደለም፡፡ ለዚህም ‹‹ነገር ግን ፂሕማችንን ላንላጭ የወንድ መልካችንን ወደ ሌላ ማለትም ሴት ወደ
መምሰል እንለውጥ ዘንድ አይገባም›› (ዲዲስቅልያ. አንቀጽ 1፣ ፍት.መን. አን.11)፡፡ ሌሎች የአፍላ የጉልምስና ምልክቶች ደግሞ
የሰውነት ጠረን መለወጥ፣ የዘር ፍሰት ወይም ሕልመ ሌሊት ማየት መጀመር ናቸው፡፡
ሕልመ ሌሊት
ለዘር የበቁ ወጣቶች
ዘር የሚከፍሉት ወይም የሚወጣቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት
ወቅት ነው፡፡ ይህ ሲሆን እንደ ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል፡፡ ይህ ባልጠበቁት ጊዜ ስከሰት በጣም ሊረብሻቸው ይችላል፡፡ ለዚህም
ግንዛቤ እንዲያገኙ እና አንደ አስደሳች ተግባር በመውሰድ እያወቁ ዘራቸውን በራሳቸው እጅ ማፍሰስ እንዳይጀምሩ የእነ አውነን በዚህ
ተግባራቸው መቀሠፍ እየጠቀሱ ኃጢአትነቱን አጥብቆ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘሌ. 15፡16 ‹‹የማንም ዘር ከእርሱ
ቢወጣ ገላውን ሁሉ በውኃ ይታጠባል
እስከ ማታም ርኩስ
ነው ዘር የነካ ልብስ ሁሉ ቁርበትም ሁሉ በውኃ ይታጠባል እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው፡፡››
ክፍል ሦስት ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment