ክፍል አስራ ሰባት
ምዕራፍ አስር
ወጣት እና አደንዛዥ ዕፀዋት
በዘማናችን የሰው ልጆች አደንዛዥና
አፍዛዥ ወይም ከመጠን በላይ አነቃቂ የሆኑ መርዛማ ዕፀዋትን ባሉበት ሁኔታ ከመጠቀም ማለትም አኝኮ ከመዋጥና ጨምቆ ከመጠጣት አልፈው
ሄደዋል፡፡ ዕፀዋቱን ንጥረ ነገር ለይተው በማውጣት በመርፌ ለመጠቀም በሚመች መንገድና በሚዋጡ እንክብሎች መልክ አዘጋጅተው ይጠቀሟቸዋል፡፡
አንዳንዶቹ ከአንድ ወር በላይ ሊያነቁ ወይም አንድን ሰው ችግሩንና ጉዳቱን እንዲረሳ ሊያፈዙት የሚችሉ ናቸው፡፡
ዛሬ ዛሬማ አደንዛዥ፣ መርዛማና
አደገኛ ዕፀዋት ከተጠቃሚዎቻቸው አኀዝ መበርከት ባሻገር በግለሰብእና በአገር ደረጃ ዋነኛ የሀብት ማግኛ መንገድ ሆነው እየተቆጠረ
ነው፡፡ በፊት በድብቅ ወደ ከተሞች ይገባ የነበሩ ዕፀዋት ዛሬ ግን በይፋ ይጫናሉ፣ በአደባባይ ይቃማሉ...፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን
ለዘመናት ስታወግዝ ኖራለች፡፡ ወደፊትም ትኖራለች፡፡
ትንባሆ ማጨስ፣ ጫት መቃም፣
ሺሻ መማግ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገቢ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም እኛ የአግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነን፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ የሚታጠነው
ዕጣን እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እንዲሁም በስጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ የሚለውን የእግዚአብሔር ሕግ መጣስ ይሆንብናል፡፡ 1ቆሮ.
6፡20፣ 1ቆሮ. 3፡17፡፡
ሲጋራ፣ ጫት እና የመሳሰሉት ሁሉ ሱስ በመሆን የሰው ልጆች በተፈጥሮ ያገኙትን
ነጻ ፈቃድ ስለሚጻረሩ ሰው ሊጠቀምባቸው አይገባም፡፡ባሪያ ያደረገን ነገር ደግሞ ከእግዚአብሔር ይለየናል፡፡ 1ቆሮ. 6፡12 ‹‹ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም፡፡›› ይህን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ ደግሞ ‹‹አእምሮንና አካልን
ሁሉ የሚጎዳና የሚገድሉ ተክሎች የተከለከሉ ናቸው፡፡›› (ፍ.ነ.አን.23፡804-807)
No comments:
Post a Comment