ክፍል አስራ ስድስት
ምዕራፍ ዘጠኝ
ዘፈንና ወጣቶች
ዘፈን
በቅኔና በግጥም ከልዩ ልዩ የድምጽ መሣሪያ ጋር እየተቀነባበረ የሚቀርብ ስልት ያለው ጩኸት ወይም ድምጽ እና የተውኔት ዲቃላ ሲሆን ዓለማውያን ሰዎች ደስታቸውን የሚገልጡበት ነው፡፡
ዘወትር ለሥጋ ፍላጎት የተሟላ ኃላፊ ፍቅርን ያወሳል፡፡ስለዚህም ፈጣሪ ሳይሆን ሰው እንዲመለክ በማድረግ የሰይጣን ተገዥ መሆን
ማረጋገጫ ነው፡፡ አሁን አሁንማ በግልጽ ሰይጣንን የሚያወድሱ ሰዎች ተነስተዋል፡፡
ዘፈን
ከአካል እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ትስስር ከመረመርክ ይጮኻሉ፣ ተንቀሳቃሽ ፊልሞችም እንዲሁ በድምጽ የታጀቡ ናቸው ለመቀስቀስ እና
ተጽእኖ ለመፍጠር ነው፡፡ ዘፈንም እንዲሁ ሰውን የመግዛት ኃይል አለው፡፡
(ሀ)
ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና (ኢሳ. 13፡21) እንዲሁም በ1መቃ. 36፡27-28 ‹‹... እየዘፈኑም
ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› እስኪ በሀገራችንም ሆነ
ሌሎች ሀገሮች ዘፋኞች ፀጉራቸውን አንጨብረውና በመጠጥ እና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛው
የባለዛሮች ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ሐዊ ትምህርት ዘፈንና ዳንስ
ከሰይጣን የተገኘ ነው፡፡ እንዲሁም የጭፈራ ዓይነት ሁሉ ምንጮች አጋንንት ናቸው፡፡
ዘፋኝነት
የሰጋ ስራ ነው፡፡ (ገላ. 5፡21) ሮሜ. 13፡13፣ 2ጴጥ. 2፡13-15፡፡ ዘፈን በዜማው፣ በግጥሙና ከእርሱ ጋር በተጎዳኘ
ባሉ ነገሮች ማለትም በስካር፣ በዳንስ፣በጭፈራ፣ በእስክስታና በአጠቃላይ ውዝዋዜን በመሳሰሉ አጋሮቹ በመታገዝ ወደ ዝሙትና ወደ
ከፋ ኃጢአት የሚያመራ ነው፡፡ ዛሬም የምናየው ይህንን ነው፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ከዚህ መራቅ አለበት፡፡ ዘፈን የሰይጣን ነው፡፡
ሱስ ወደመሆን ያድጋል ያን ጊዜ መላቀቅ ይከብዳል መንፈሳዊነትን ይጋፋል፤ ለጸሎት ለመዝሙርና ለምስጋና፣ ለመንፈሳዊ ነገር ያለን
ፍቅርና ትጋት እንድበርድ ያደርጋል፡፡ ከዚያም የረከሱ የአጋንንት ማደርያ ያደርጋል፡፡ (1ሳሙ. 16፡23) ንጉሡ ሳዖል ላይ
ያደረው አጋንንት በደዊት በገና ይርቅ ነበር፡፡
የዘፈን
አድማጭ የዘፈን ተባባሪ ነው፡፡ዘፋኙ ዘፈንን ከውስጡ በአንደበቱ አማካኝነት አውጥቶ ለሌሎች ያጋራል፡፡ አድማጩ ደግሞ በጆሮው
ይጋራል፡፡ እንደውም የአድማጩ ይብሳል፡፡ ስለዚህ ዘፈን ባለመስማት ከፈለግን ልባችንን ለዘፈን መስጠት አያስፈለግም፡፡ መስማት
እና ማዳመጥ ይለያያልና፡፡ በዘመናት ዘፈን ጎጂ እንጂ ጥቅሙ ታይቶ አያውቅም ስለዚህ እንዝፈን አንስማ፡፡ (ዘፍ. 4፡21፣
መሳ. 16፡23-31፣ ዘጸ. 17፡31)
የመናፍቃን መዝሙር
ዘፋኝነት
እና ዘፈን መስማት ለመንፍቃን መዝሙር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የመናፍቃን መዝሙር ከሚያስጨፍር ዘፈን አይለይምና፡፡ዘፈን
መስማት ኃጢአት ነው የመናፍቃንን መዝሙር መስማት ግን ዓመፅና ክህደት ነው፡፡ ለዚህ እኮ
ነው ብዙ ዘፋኞች ወደ መናፍቃን የሚሄዱት ዋና ስራቸው ግጥም መቀየር ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ሁለቱም የአጋንንት ስለሆኑ ማለት ነው፡፡
የክርስቶስ ስም ስለተጠራበት አትመን ክርስቶስ አይደለም፡፡ በክርስቶስ ስም የመጣ የሠይጣን ትምህርት እና ተቋም ማኅበር ነው፡፡
ብዙ ዕውቀት ለማግኘት እነዚህን አንብባቸው (1ቆሮ. 10፡18፣ ኤፌ. 4፡5፣ 2ቆሮ. 11፡13፣ ዘጸ. 23፡13፣ 2ቆሮ. 11፡14-15)፡፡
ዘፋኝነት የአደባባይ ኃጢአት ነው ቤተ ክርስቲያንም ታወግዛለች፡፡ የተጠመቀ ሁሉ
ከዘፈን የተለየ መሆን አለበት ክርስቲያን ሆኖ ዘፋኝ የለምና፡፡ ዛሬም ብዙዎች በዚህ ሕይወት ሲኖሩ እንመለከታለን ትክክል ግን አይደለም፡፡
ዘፋኝ እና ዘማሪ መሆን አይቻልም፣ ዘፋኝ እና ክርስቲያን መሆን አይቻልም፡፡ በሕዝብ ፊት ዘፋኝነትን ትተናል ብለው ከተመለሱ ብቻ
ቤተ ክርስቲያን ትቀበላቸዋለች፤ ማስተማሯን ግን አታቋርጥም፡፡ ካልሰመዋት ግን እግዚአብሔርን ትተው የዘፈን አባት የሆነውን ሰይጣንን
ሰምተዋልና ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላሉ፡፡ ገላ. 6፡7፣ 1ሳሙ. 15፡22፣ ሮሜ. 2፡3
No comments:
Post a Comment