ክፍል አስራ አራት
.... የቀጠለ....ስለ መዝናናት እና መደሰት
ሲኒማና ቴሌቪዥን
ተንቀሳቃሽ ስዕል ፊልም
ይባላል፡፡ በሲኒማ የምናያቸው ነገሮች ተዋሕደውን የኛ አንድ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ፊልም ላይ ያየኸውን ለጊዜው ልትጠላው ትችላለህ፡፡
ነገር ግን አንድ ቀን በቅጽበት ማሰብ ትጀምራለህ፡፡ ሰይጣን ደግሞ ልዩ ልዩ የኃጢአት ሥራዎችን እንድትመለከት በር ይከፍታል፡፡
ወደፊት በምዕራባውያን
የሚሠሩ ፊልሞች የሀገራችንን የማይውጥበት ምክንያት የለም፤ አሁንም እያየን ስለሆነ፡፡ ብዙ ፊልሞች ትዕቢትን፣ የዘር ልዩነትን፣
አድልዎን፣ ጭካኔንና ግፍን፣ ቅንጦትን፣ ግለኝነትን፣ የራስ ጥቅምን ማስቀደምን፣ የሥልጣን ሽሚያንና ስግብግብነትን፣ ምንዝርን፣ ዝሙትን፣
ግብረ ሰዶምን፣ ዓመፅን፣ ስርቆትን፣ ቂምንና የሕዝብ መጨፍጨፍን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ፊልም የሰው ልጆችን ሊጎዳ የሚችለው በብዙ አቅጣጫ ነው
(ሀ) መጥፎ ድርጊቶችን የሚያንጸባርቁ ፊልሞችን ደጋግሞ ማየት ውጤቱ
ያው ነው፡፡ መተሻሸት፣መተቃቀፍ፣ ብዙ ተራክቦን የሚያሳይ ካየህ ለፍትወት መነሳሳትህ አይቀሬ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በደልክ ማለት
ነው፡፡
(ለ) በፊልሙ ላይ ከሚታዩት ዓይነት ሰዎች ጋር እንደዋለ ያህል ሊቆጠር
ይችላል፡፡ መዝ. 17፡26 ‹‹ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ፡፡››
(ሐ) ምንም እንኳን
በተግባር ባትፈጽመውም ክፉ ነገርን በደስተኛ ልብ መቀበል በራሱ መርከስ ነው፡፡ በሥጋ የሚፈጸመው በልቡና ወጥቶ ወርዶ የተወሰነ
ሐሳብ ነው፡፡
(መ) ዝሙት የሞላባቸውን ፊልሞች መመልከትህ ወደ ክፉ ኃጢአት ይወስድሃል፡፡
አጠገብህ ሰው ስለሌለ የዝሙት ፊልሞችን ታይህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የማታየው እግዚአብሔር ካንተ ጋር መሆኑን አትርሳ፤ ቅዱሳንም
በዙሪያህ ናቸውና ተው ይቅርብህ፡፡
(ሠ) ፊልምን አዘወትሮ መመልከት ሱስ የመሆን ባሕርይ አለው፡፡ 1ቆሮ.
6፡12 ‹‹ሁሉ ተፈቅዶልኛል አንድስ እንኳን በእኔ ላይ አይሰለጥንብኝም›› ጊዜን ማጥፋት፣ ነገሮችን ችላ ማለት ይከተላሉ፡፡
(ረ) በፊልም ያዩትን
በትዳራቸው በመተግበር ትዳራቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሰዎች አሉ፡፡
(ሰ) ፊልም አዘወትሮ
መመልከት እንደ ፊልሙ ተዋናይ የመኖር ምኞትን በማሳደር ተግቶ በመሥራት የማግኘት ወኔን ይሰልባል፡፡ ወጣቶች በሕልም ዓለም እንዲኖሩ
ያደርጋቸዋል፡፡
(ሸ) ፊልም ወጣቱ
ሁሉን ነገር ያለ ረድኤተ እግዚአብሔር ለማግኘት የሚያስቡ ትዕቢተኞች ያደርጋቸዋል፡፡
(ቀ) ፊልም ዘወትር
የሚመለከት ወጣት ነጻ ተመልካች መሆን አይችልም፡፡ እርሱ ራሱ በአንድ አቅጣጫ በፊልሙ ውስጥ ይተውናል፡፡
(በ) መልካም ነው
ከተባለው ፊልም እንኳን ባላሰብከው መንገድ አንድ መልካም ባሕርይህን ታጣለህ፡፡ ሌብነትን፣ ዝሙትን፣ ጉልበተኛነትን፣ ውሸትንና የመሳሰሉትን
ሳታወድስ አትቀርም፡፡መዝ. 9፡23
ምክር፡- እኛ ክርስቲያኖች
ዓለማውያን ፊልም የሚሠሩት ገንዘብ ለማግኘት እና የሠይጣንን አሰራር ማሰረጨት ስለሆነ ልንርቀው ያስፈልጋል፡፡ ከዘፈን ይበልጥ የሰውን
ሕይወት ወደ ክፉ ጎዳና ሊወስድ የሚችል እንደሆነ የሚካድ አይደለም፡፡ ብዙ ለማግኘት ብለው ፊልም የሚያከራዩ ክርስቲያኖችም አሉ
ግን ይህ ስራቸው ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጋር አይሄድም፡፡ ስለዚህ ከወዲሁ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ከፊልም ሱስ ነጻ ለመሆን መጀመሪያ
ከፊልም ጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያዘነብል ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የቀረውን ደግሞ ከ‹‹ሕይወተ ወራዙት ክፍል 2 አንብብ፣ ንስሐ አባትህን
አማክራቸው››
No comments:
Post a Comment