ክፍል አስራ አምስት
ምዕራፍ ስምንት
ወጣት እና የሚያሠክር መጠጥ መጠጣት
... መጽሐፍ ቅዱስ
መስከርን እና ለብዙ የወይን ጠጅ መጎምጀትን እንጂ በልክ መጠጣትን አይቃወምም፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን በቃና ገሊላ በእናቱ
አማላጅነት ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ የለወጠው፡፡ክርስቶስ ለውጦ የሰጣቸው የወይን ጠጅ አልኮልነት የሌለውና የማያሳክር ሆኖ አይደለም ነገር ግን ልካቸውን አውቀው መጠጣት የሰዎቹ ድርሻ ነው፡፡
ዛሬም ቢሆን ወጣቶች መጠጥ ሲጠጡ አእምሮኣቸው እስኪስት ድረስ መጠጣት ኃጢአት ነው፡፡ ምክንያቱም መስከር ያስቀጣልና፡፡በአግባብ
ከተጠጣ መልካም መሆኑን ሲገልጽ ቅዱስ ጳውሎስም የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ ሲጽፍ ‹‹ስለ ሆዲህ ስለ ብሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ
ጠጣ፡፡›› (1ጢሞ. 5፡23) በሌላ መልኩም ወይን በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም ይቀርብ ነበር፡፡ ማቴ. 26፡17-29፣ ሉቃ.
10፡34፣ ጦቢ. 4፡15፣ ሲራክ. 34፡24-26፣ ቲቶ. 2፡3፣ 1ጢሞ. 3፡8፡፡ እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡ ስለ መጠጥ
ብዙ ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡ ለማንኛውም ግን ሁሉም ነገር በግባብ ካልሆነ ጉዳቱ የከፋ ነው፤ መጠጥም እንዲሁ፡፡
የአልኮል መጠጥ የሚያስከትለው ጉዳት
መጠጥ ከመጠን በላይ ከሆነ ያሰክራል፡፡
የሚገርመው ደግሞ ሰው ከመጠን በላይ መጠጣቱን ና መስከሩን እንኳን ላይገነዘበው ይችላል፡፡ የስካርን ጉዳት ሲገልጽ ‹‹ዋይታ ለማን
ነው? ኀዘን
ለማን ነው?
ጠብ ለማን
ነው? ጩኸት
ለማን ነው?
ያለ ምክንያት
መቍሰል ለማን
ነው? የዓይን
ቅላት ለማን
ነው? የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ይፈትኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን? ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት በቀላ ጊዜ፥ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ፥ እየጣፈጠም በገባ ጊዜ።
በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል።ዓይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል።›› (ምሳ. 23፡29-33)
ስካር
ማስተዋልን ያሳጣል፤ የራስን ተድላ እንጂ የሌላን አያሳስብም፡፡ ሰካራም ስለማያስተውል የተመከረውን በሙሉ አይሰማም ይረሳል፡፡
ሰው ከሰከረ ሕዋሳቱ እንደማይቀናጁለት ሁሉ አእምሮውም በትክክል አያስብም፡፡ አዝወትሮ የሚሰክር ከሆነ ደግሞ የአእምሮ ስራ
ይዛባል፡፡ ለዚህ ነው ነብዩ ሆሴዕ ‹‹ግልሙትናና የወይን ጠጅ
ስካርም አእምሮን
ያጠፋል›› (4፡11) ያለው፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሶሎሞን በምሳሌው ‹‹የወይን ጠጅ
ፌዘኛ ያደርጋል፥
ብርቱ መጠጥም
ጠበኛ ያደርጋል፤
በዚህም የሳተ
ሁሉ ጠቢብ
አይደለም›› (ምሳ. 20፡1) ሉቃ. 21፡34፡፡
ስካር
ወደ ዝሙትና ወደ ጉልምትና ነው የሚያመራው፡፡ ይህም ጠቢቡ ሶሎሞን እንዲህ ይላል ‹‹ወደ ወይን
ጠጅ አትመልከት
በቀላ ጊዜ፥
መልኩም በብርሌ
ባንጸባረቀ ጊዜ፥
እየጣፈጠም በገባ
ጊዜ። በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል። ዓይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል›› (ምሳ.
23፡31-33)፡፡ አንድ ነገር ልንገራችሁ በየመጠጥ ቤቱ የሚያስተንግዱ እህቶች መስፈርታቸው ወንዶችን በዝሙት መሳብ የምትችል
መሆን አለባት፡፡ ሎጥ ላይ የደረሰውን ማስታወስ ግድ ይላል፡፡ በኃጢአት ምክንያት ሰዶም እና ጋሞራ ሲጠፉ ሚስቱም፣ ልጆቹን
ሊያገቡ የሚችሉ ወንዶችም ጠፉ፡፡ ነገር ግን ልጆቹ በወይን ጠጅ አስክረውት ከእርሱ ጋር ተኝተዋል፡፡
ስካር
የስጋ ስራ እንጂ የመንፈስ አይደለም፡፡ (ገላ. 5፡19፣ ሮሜ. 13፡13) ንስሐ ካልገቡ የስካር መዘዙ በምድር ብቻ የሚቀር
አይደለም ‹‹ሰካራሞች የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› (1ቆሮ. 6፡10)፡፡ እንዲሁም ኢሳ. 28፡1-8፣ ምሳ.
23፡29፣ ኢዮ. 1፡5፡፡ሌሎችንም በዚህ መልኩ እናስብ የጤና፣ ሱስ፣የሰላም፣ የወጭ...፡፡ሌላውን ከሕይወተ ወራዙተ ክፍል 2
ያንብቡ፡፡
No comments:
Post a Comment