ክፍል አራት
1. ግብረ አውናን
ሕልመ ሌሊት ወጣቶች በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ በሚያልሙበት ጊዜ ስለሚከሰት የ‹‹ፈሳሽ ነገር›› ከሰውነት መውጣት ነው፡፡
ነገር ግን በወጣትነት ወራት ስለ አባለ ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና ለተቃራኒ ጾታ የሚኖር ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ከእንቅልፍ
ውጭ ንቁ በሆኑበት ሰዓት በስሜት እስኪረኩ ድረስ የጾታ ብልቶቻቸውን በመነካካትና በማሻሻት ለመደሰት የሚሞክሩ ወጣቶች አሉ፡፡ ይህ
ድርጊት በአብዛኛው በስውርና በግል ስለሚፈጸም በዚህ መጥፎ ልማድ የተለከፉት ወጣቶች መካሪ ሳያገኙ ልማዳቸው አብሮአቸው ያድግና
ለወደፊት ለኑሮአቸው ከባድ እንቅፋት ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር መላእክትን በተለያየ የምሕረት ግዴታዎች ቅዱሳን እንዳሉት ሁሉ በልዩ ልዩ መንገድ ሰውን እንዲፈትኑ ድርሻ
ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አግንንት አሉት፡፡ ከእነርሱም ውስጥ አንዱ ‹‹ሰይጣነ ዝሙት›› ነው፡፡ ሮሜ. 9፡22፡፡ ሰይጣነ ዝሙት የሰው
ልጆችን የሚፈትኑበት መንገድ ረቂቅና ልዩ ልዩ ነው፡፡ አንዳንዶች የፈተና ስልቶች ፈጽሞ ከዝሙት ጋር ምንም ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም፡፡
ነገር ግን ላስተዋለ ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸው ናቸው፡፡አባቶቻችን ግን ይህን የሰይጣንን ሽንገላ በሕይወታቸው ስለተረዱት መንፈስ ቅዱስም
የገለጠላቸውን ጽፈውልን አልፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡ ለምሳሌ ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚሳብባቸው
መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው (መሻሻት፣ መነካካት፣ መዳበስ ማለት ነው)፡፡
ሕዝቅ. 23፡8 ‹‹ግልሙትናቸውን አፍሰውባት ነበር›› ማለት ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፉና ሲዳሩ ሩካቤ
ሳይፈጽሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ ነው፡፡ እንዲሁም በሕዝቅ. 23፡3 ‹‹የድንግልናዋን ጡቶች ዳብሰው ነበር›› እንዲህ በማድረግ
ጥሩ የእህትነት ወይም ወንድማዊ ቅርርቦሽ በማስመሰል እየተሻሹ የወንድ ዘር ወይም የሴት ዘር የሚያፈሱ አሉ፡፡ ይህም በመኪና ውስጥ፣
በሰልፍ ላይ፣ ሰላምታ ስለዋወጡ... ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡
W ወጣቶች ይህን የሚያደርጉት
አስበውበት ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ልዩ ዘዴ በመፍጠር ምንም ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገለባበጡና
እያንኮራፉ በልዩ ልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው ለመተኛት የተገደደችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ፡፡ ይህ ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር የትም
ከሚፈስባቸው ሕገ ወጥ መንገዶች አንዱ ነው፡፡
W ሌሎች ደግሞ በአድካሚ
ጉዞ ወቅት ደጋፊ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ፣... ወዘተ እየመሰሉ ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመዳበስ የሚሞክሩ
ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ውጫቸውን ላየ አዛኝ ሌላውን ለመርዳት የሚፋጠኑ ይመስላሉ፡፡ ይህ ችግሩ ወንዶች ይህን በሚያደርጉበት
ጊዜ ልባቸው በፍትወት እሳት እንደ ሰም እየቀለጠና አባለ ዘራቸው እየፈሰሰ መሆኑ ነው፡፡ ሰውን ለመርዳት የሚፋጠኑትም ፍትወታቸው
እስክትሟላላቸው ድረስ ብቻ ነው፡፡
W አንዳንዶች ደግሞ እነርሱ
ለመነካካት ፈጽሞ እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ችግር አንደገፉ ወይም እንዲገፋፉ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይጥራሉ፡፡ ይህ የሚሆነው
በአብዛኛው ሕዝባዊ ስብሰባዎች በሚደረጉባቸው ዕለትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው፡፡ ለምሳሌ በጥምቀት እና መስቀል በዓላት፣
የተለያዩ የንግስ በዓላት ላይ፣ የሕዝብ አውቶብስ ላይ ይከሰታል፡፡ ስለዚህ በአንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ላይ ከሌባ ብቻ ሳይሆን ሕዋሳትን
ከሚዳብስ ሴሰኛም ራሳችን ልንጠብቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ሌባ የራሱ ያልሆነውን የሰውን ገንዘብ ይሰርቃል ይህ ዓይነቱም የራሱ
ያልሆነውን የሰውን አካል ይነካካልና፡፡ ባሁኑ ጊዜ የሚነካካውም ሆነ የሚነካውም የሚደሰትበት ዘመን ላይ ነን፡፡
W ሌሎች ደግሞ ውጫዊ
ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን ለማፍሰስ የመርካት ተግባር የማይጠረጠሩ ዓይነት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ዕድሜያቸው በጣም የገፋ፣
በአስተሳሰብ የበሰሉ፣ አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች የሌሎችን ሕዋሳት ለመነካካት
የሚያደርጉት ጥረት ‹‹ይህን አስበው አይደለም›› እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል፡፡ ነገር ግን ተው ይቅርብን እንደዚያ
ዓይነት ነገር የለም፡፡
W ሌሎች ደግሞ በተለይ
በሰንበት ትምህርት ቤት እና በግቢ ጉባኤያት ላይ የሚታየው ጥሩ እህት እና ወንድም በመምሰል በሠላምታ ጊዜ ወጣ ያለ መተቃቀፍ፣
እጅ ለእጅ ተያይዞ መሄድ፣እጅ ትከሻ ላይ መጫን እና ወገብ ይዞ መሄድ እና የመሳሰሉት ይታያሉ፡፡ ይህ ለጊዜው ክርስቲያናዊ ፍቅር
የሚመስል ነገር ግን በውስጡ ለፍትወት የሚውልበት ጊዜ ሰፊ ነው፡፡ የወንድ እና የሴት ሰውነት ስነካካ ፍትወትን መቀስቀሱ አይቀርምና
በገደብ እናድርገው፡፡ እውነተኛ ፍቅር በልባችን ካለ ብዙ የፍቅር መገለጫዎች አሉና በእነዚያ እናድርግ፡፡ በግቢ ጉባኤያት እና ሰንበት
ትምህርት ቤት ላይ ሰው ወረተኛ የሚሆነው ለምን ይመስላችኋል? ገና እንደተለያየን የምንረሳሳው ለምን መሰላችሁ? እስኪ ዝም ብላችሁ
አስቡ መንገድ ለመንገድ ተቃቅፈን ስንጓዝ፣ አንገት ለአንገት ተቃቅፈን ሠላምታ የምንለዋወጠው ለእውነተኛ ፍቅር ነው? መልሱን ለራሳችሁ
ይሁን፡፡
W ሌሎች ደግሞ ታዳጊ
ሕጻናት በማባለግ የወንድ ዘር ያፈሳሉ፡፡ በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕጻናትም የእነዚህ ሰዎች ጥቃት ሰለባ ናቸው፡፡ ይህም ሕጻናቱን
በመሳም (አፋቸው ውስጥ)፣ ሀፍረተ ስጋቸውን በመዳበስ ወዘተ ናቸው፡፡ሕጻናቱ አነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያሰተውሉትም፣
አያውቁትም፣ ቢያውቁትም አይቃወሟቸውም፣ አይከሷቸውምም ወይም በትንሽ ነገር በቀላሉ ሊባበሉና ሊታለሉላቸው ይችላሉ፡፡ ሕጻናቱ ጉዳቱ
ስለማይታያቸው ያ የሚዳብሳቸውን ሰው ይወዱታል፣ ደስ ስለምላቸው፡፡ ሕጻናትን ያጫወቱ፣ ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፉ በፍትወት
እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር የሚለውሱት ብዙ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት እኮ ብዙ ሕጻናት ተደፍረዋል እየተባለ በተለያየ ሚዲያ የምንሰማው፡፡
ባሁኑ ጊዜ የሚታገቱ ሕጻናት፣ በጉድፈቻ መልክ የሚሰበሰቡ ያለ እድሜያቸው ወሲብ የሚፈጸምባቸው እና ለግብረ ሰዶምነት የሚዘጋጁ ናቸው፡፡
ጥያቄ
W ሕጻን ሴት ከእናቷ ይልቅ አባቷን የምትቀርበው ለምን ይመስላችኋል?
W
ሕጻን ወንድስ ከአባቱ ይልቅ ለእናቱ የሚቀርባት ልምንድነው?
ካላይ ያለውን ግንዛቤ በማንም ሰው ቢሆን ያለ አግባብ እንዳንተማመን የሚረዱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የምንውልበትን፣
የምንጓዝበትን፣ የምናድርበትን ቦታ ዚሪያውን እየቃኘን ወደ ዝሙት የሚመሩ ምክንያቶችን ከወዲሁ አውቀን እንድንሸሽ ያግዘናል፡፡ አንዲሁም
ሕጻናቶቻችንን በጥንቃቄ እንድንይዝ የሚያደርጉን ሲሆኑ በዚህ መጥፎ ተግባር የተመረዙትን ሰዎች ደግሞ ስራቸው በብዙዎች ዘንድ መገለጡን
አውቀው አደብ እንድገዙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡
ሠይጣነ ዝሙት አንድን ሰው ያልተፈቀደለትን የሌላን ሰው አካል በዝሙት
መንፈስ ለመንካት እንዲመኝ እንደሚያነሳሳ ሁሉ ሰውዬው የራሱንም ሕዋሳት
በዝሙት መንፈስ ሆኖ እንድደባብስ የሚገፋፋበት ጊዜ አለ፡፡ ሰይጣኑ ሰው የራሱን ሰውነት ያለ ማቋረጥ እንዲያክ፣ እንዲያሻሽ አንዲደባብስ
በማድረግ የራሱ ሰውነት እንዲሸክረውና እንዲኮሰኩሰው በማድረግ ፈተና ያመጣበታል፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ሰውነቱንም
የሚያሻክርበት ጊዜ አለ፣ ያለ ማቋረጥም አንዲያክ ያደርገዋል፡፡ አንተም ስለዚህ በቆምክ ጊዜ ሕዋሳትህን ትዳብሳለህ፣ ትንጠራራለህ፣
ወይም ትወጣጠራለህ፣ እግርህንም ታፋትላለህ፡፡ ይህ ርኩስ መንፈስ ለመጀመሪያ ማሳከክ ሲጀምርና ሰውነትህን እንድትደባብስ ሲያደርግ
ከሕዋሳቶችህ የሚመርጠው የለም፡፡›› ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውዬው የሰይጣን ፈተና መሆኑን ካልተረዳ እንዲያው እንዳሳከከው ወይም ሰውነት
እንዲቆሸሸ ያስባል፡፡ ገፋ ካለም ወደ ሐኪም ዘንድ ይሄዳል፡፡ ሰውነት በማሳከክ የጀመረው ሰይጣነ ዝሙት ዓላማውን ከግብ ለማድረስ
በዚህ ብቻ አይወስንም፡፡ እንደ መጽሐፈ መነኮሳት ገለጻ ወደ አባለ ዘሩም ይሄድና ያን ሰው ያለመጠን እንዲያክ ያደርገዋል፡፡ ያንን
ሰው በዝሙት ሐሳብ ተስቦ በዚህ መልኩ ብልቱን እያሻሸ ዘሩን እስኪያፈስ ድረስ ዕረፍት ሳይሰጠው ፈተናውን ያስቀጥላል፡፡
ማስገንዘቢያ፡- ከዚህ አንጻር ማሳጅ እና ፊዚዮ ቴራፒ ዓላማው ከዚህ ጋር የተያየዘ ነው፡፡ ሰይጣነ
ዝሙት ሰው የገዛ ሰውነቱ እንድከብደው በማድረግ እንዲታሽ ያደርጋል፡፡ ለዚህ መፍትሔው ስግደት፣ ጾም እና ጠበል መጠመቅ ነው፡፡
በዚህ ዓይነት የዝሙት ዝንባሌ ተይዞ ከእንቅልፍ ውጭ ዘር እያወቁ ወደ
ውጭ ማፍሰስ ግብረ አውናን ይባላል፡፡ አውናን የተባለ ሰው ከሚስቱ ጋር ተኝቶ ሳለ ዘሩን ከሚስቱ ማኅፀን ውጭ ያፈሰው ስለ ነበር
ነው፡፡ ዝሙትን ወዶ ክቡር ዘርን የትም ማፍሰስ የአውናን ዘሩን ከማህፀን ውጭ መፍሰስ አንድ ናቸውና፡፡ ዘፍ. 38፡9
ግብረ አውናን ፈጽሞ ተገቢ አይደለም፡፡ ገበሬው ዘሩን በጎተራ አቆይቶ
ያለቦታው፣ ያለጊዜው እንደማይበትነው ሁሉ የሰው ዘር በሰውነት ተጠብቆ መቆየት አለበት ከጋብቻ በኋላ በሩካቤ ጊዜ በመልካሟ ማሳ
በሚስት ማኅፀን መዝራት አንጂ በልዩ ልዩ ምክንያት ሆን ብሎ ዘርን እንደ ጉድፍ ከማኅፀን በአፍአ ማፍሰስ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡
የሰው ዘር ክቡር በመሆኑ ዘራቸውን በሜዳ ከሚያፈሱ ሰዎች ይልቅ ሰው
የመሆን እድል የነበራቸው ነገር ግን በየሜዳ ፈሰው የቀሩት ዘሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ዘር ያፈሰሱ ከሕገ እግዚአብሔር ሲወጡ፤ የፈሰሰው
ዘር ግን ምንም ካለመበደላቸውም ቢወለዱ ኖሮ ጳጳስና ንጉሥ የመሆን ዕድል ሊኖራቸው ስለሚችል ነው፡፡ በዝያን ጊዜ ዘር ያፈሰሱትን
ጊዜ ሳይሰጣቸው እግዚአብሔር ቀስፏል፡፡ ዘፍ. 38፡9-10 (ከመጽሐፍ ቅዱስ ሳያነቡ አይለፉ)
መፍትሔው ደግሞ ‹‹እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ አንዚህም
ዝሙትና ርኩሰት፣ ፍትወትም ክፉ ምኞትም፣ ጣኦትንም ማምለክም የሆነ መጎምጀት ነው፡፡›› (ቆላ. 3፡5)ነው፡፡ ብልቶቻችሁን ግደሉ
ማለት አትቀስቅሱ ማለት ነው፡፡ ዘርን ማፍሰስ ከጣኦት አምልኮ፣ ከክፉ ምኞት፣ ከርኩሰት፣ ከመጎምጀት ጋር ተሰልፎ እየተቆጠረ እንዴት
ተገቢ ሊሆን ይችላል፡፡ በኤፌ. 4፡19 ‹‹ደንዝዘውም በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ፡፡››
የሚለው ግብረ አውናን ለሚፈጽሙ ሰዎች ሊጠቀስ ይችላል፡፡
በፍትወት ለተቃጠሉ ሰዎች ‹‹በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን
መግዛት ባይችሉ ያግቡ፡፡›› ይላል፡፡ (1ቆሮ. 7፡9) ስለዚህ በዝሙት ለሚቃጠሉ መፍትሔው ማግባት እንጂ መሰንጋት (ሴጋ መፈጸም)
አይደለም፡፡ ግብረ አውናን ምንም ዓይነት ኃላፊነት ሳይሸከሙ ያንን እርካታ ለማግኘት እንደመሞከር ይቆጠራል፡፡ የምኞት ቃጠሎን ዘርን
በማፍሰስ ለማብረድ መሞከር ስሕተት ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ነገር ሲያጋጥም ተቋቁሞ በማለፍ ፈንታ በተሳሳተ ጎዳና በመጓዝ ችግሩን
ለማምለጥ መሞከር ጽንፈትንና ደካማነትን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህን ዓይነት የለመደ ወጣት ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ከመመከት ይለቅ
ሌላ የተሳሳተ አቋራጭ ሲማትር ይገኛል፡፡በዚህ ምክንያት ብዙ ወጣቶች ላለመማራቸውና ለሥራ አጥነታቸው ወይም በሕይወታቸው ለገጠማቸው
አንድ ችግር ተገቢና ጤናማ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ዱርዬነት፣ ሌብነትን፣ ሰካራምነትን፣ ስጋራ ማጨስንና ጫት መቃምን እንደ አማራጭ
ይወስዳሉ፡፡
ማቴ. 5፡19 ላይ ሰይጣንም ቢሆን ሐሳቡ እስከሚፈጸምበት ድረስ በትንሽነቷ
ንቀን እንድንፈጽማት ከግብረ ሰዶምና ከዝሙት ታንሳለች በማላት ያሳስበናል እንጂ በዚሁ ኃጢአት የተያዙትን ሰዎች ደግሞ ያልሠሩትን
ግብረ ሰዶምና ዝሙት እንዲሠሩለት ‹‹አንደኛውን ዝሙት ይሻላል፣ ይህን የመሰለህ ኃጢአት እየፈጸምህ ዝሙት አልሠራውም ለማለት ነው?››
እያለ ተስፋ ለማስቆረጥ እንደሚያምታታቸው መዘንጋት የለብንም፡፡
ዛሬ በዓለማችን ላይ ሴጋ የሚፈጽሙ ወንዶች ብቻ አይደሉም ሴቶችም ጭምር ናቸው እንጂ፡፡
በእድሜ ደረጃም በሰባዎቹ የሚገኙ ሽማግሌዎች እና አሮጊቶችም ይፈጽማሉ፡፡ በቁጥር ሲገለጽም 2/3 ወጣት ልጃ ገረዶች፣ 95 በመቶ
ወጣት ወንዶች፣ 33 በመቶ በሰባዎቹ እድሜ የሚገኙ አሮጊቶች እና 43 በመቶ የሚሆኑ ደግሞ ሽማግሌዎች ይህን ተግባር ይፈጽማሉ፡፡
ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment