በእንተ ርእስየ

Friday, March 25, 2016

ከፊት ይልቅ ትጉ (2ጴጥ. 1፡10)

የዚህ ጽሑፍ መነሻ አላማው በከርስትና ሕይወት የምንኖር እኛ ክርስቲያኖች ባለን ሕይወታችን ይልቁን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ዕለት ዕለት ማደግ እንዳለብን ለማስረዳት ነው፡፡ቃሉን የተናገረው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሆን የተናገረውም በሁለተኛ መልእክቱ ላይ ነው፡፡ ሙሉ አንቀጹ እንዲህ ይላል፡- ‹‹… ስለዚህ ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ … እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፡፡›› ይላል፡፡
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር ምሳሌና አርአያ ነው፤የሚያድገውም እግዚአብሔርን ወደ መምሰል ነው፡፡እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ሰውም ወደ ቅድስና ሕይወት ያድጋል፡፡ ዘወትር በእምነቱ እያደገ መምጣት አለበት ለዚህ ነው ቅዱሳን በእምነታቸው ጸንተው በምግባር በርትተው አስር ማዕረጋት ውስጥ ያልፋሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት እነርሱ በርትተው እግዚአብሔር እያገዛቸው ከአንዱ የቅድስና ማዕረግ ወደ ሌላ ማዕረግ ያልፋሉ (ያድጋሉ)፡፡ ቅዱሳን ከፊት ይልቅ እየበረቱ ካለፈው እየተማሩ ለሚመጣው እየተዘጋጁ ይተጋሉ፡፡ በኀጢአት ቢወድቁ እንኩዋን ተስፋ ሳይቆርጡ ‹‹ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና ይነሳማል ኀጢአን ግን በክፉ ላይ ይወድቃሉ›› ምሳ. 24፡16 የሚለውን በማስተዋል ይተጋሉ፤ይጋደላሉ፡፡ በመትጋታቸውም እግዚአብሔር ለክብር ያበቃቸዋል፡፡
እኛ በዘማናችን ክርስትናን ከትላንት ይልቅ ዛሬ በተለየ መልኩ እምነታችንን እያሳደግን መሄድ አለብን፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ለዚህ ነበር ምእመናን በእምነት መጽናት እንዳለባቸውና ከፊት ይልቅ መትጋት እንዳለባቸውና ይህን ሲያደርጉ ደግሞ በሕይታቸው መሰናክል እንደሌለ ይመክራቸዋል፡፡
በትምህርቱ ውስጥም እግዚአብሔር ህዝቡን ወደ ራሱ በተለያየ መንገድ እንደሚጠራቸውና ይህንን ጥሪ ማጽናት የሚችሉት ግን ከፊት ይልቅ ሲተጉ ብቻ እንደሆነ ነው፡፡እግዚአብሔር ሁላችንንም በተለያየ መንገድ ጠርቶናል በከፍተኛ ትምህርተ ተgማት ትምህርታችን ጎን ለጎን ቃሉን እየሰማን እየተማርን እንድናገለግለውም ፈቅዶልን ነበር ነገር ግን ያ የትላንቱ አገልግሎት እና ትምህርት ዋስትናችን የሚሆነው ዛሬም ዘወትርም ወደፊትም ስናገለግል ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ጌታችን እስከመጨረሻ የጸና እርሱ ይድናል ያለው፡፡ ማቴ. 24፡13 ካልሆነ ግን ለፍርድ ይሆንብናል፡፡ እኛም በግቢ እያለን የነበረን ትጋት፣ፍቅር፣ሀሳብ፣አንድነት፣የአገልግሎት ተነሳሽነት፣የንስሀ ሕይወት፣የቁርባኑ ሕይወት፣ከራሳችን ተርፈን ለሌሎች እንሆን የነበርን እኛ ዛሬስ ዬት ይሆን ያለነው? ነበርን ከማለት ወጪ እውነት ከፊት ይልቅ ተግተን ይሆን? በትዝታ ነው ወይ በእውነት ነው እየኖርን ያለነው? የሚድነው ግን እስከመጨረሻ የጸና እና ከፊት ይልቅ የተጋ ነው፡፡ ከቤተክርስቲያን ርቀን ወይስ እንደበፊቱ በአገልግሎት ስፍራ ነን? በነገር ሁሉ የረዳንን እግዚአብሔርንስ እናመሰግነው ይሆን? እግዚአብሔር ግን የቀደመው ፍቅራችንን ይፈልጋል ካልሆን ግን ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን መልአክ እደተጻፈለት ‹‹…የሚነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና›› ራዕ. 2፡4፡፡ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር የሚታወቀው ስናገለግል፣ስናመሰግን … ከፊት ይልቅ ስንተጋ ነው፡፡ እውነት እንደ ድሮ በቤቱ ነን ወይስ አለምን መስለናል? መጽሐፍ ግን እንዲህ ይላል ‹‹ በልባችው መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህችን አለም አትምሰሉ›› ይላል፡፡ አለምን መምሰል ሞት ነው፤ ምድራዊ ነው ሰማያዊ ዋጋ አያሰጥም፡፡ ሮሜ. 12፡2፡፡
ሰው በክርስትና ሕይወት እያደገ ካልሄደ የከፋ ውድቀት ይወድቃል በመንፈሳዊ ህይወቱ እየዛለ መንፈስ ቅዱስ እየራቀው ጥበብ እና ማስተዋል እየተለዪት ይሄዳል፡፡ ለዚህ መፍትሔው ከፊት ይልቅ መትጋት ነው፡፡ በስጋዊ ኑሮውም ይሁን በመንፈሳዊ ህይወት እየተሻሻለ፣እያደገ መሄድ አለበት፡፡ ይህም በዓለማዊ ኑሮው ኃላፊነት እየጨመረ ይመጣል ለሀገር፣ለቤተሰብ፣ለህብረተሰብ የሚያበረክተው፣የሚሰጠው እገዛ፣አገልግሎት እየላቀ መሄድ አለበት፡፡ ትላንት ተማሪ የነበረ ዛሬ መምህር፣ ትላንት ጠያቂ የነበረ ዘሬ እና ወደፊት ተጠያቂ በአጠቃላይ ከፊት ተሸሎ መገኘትን ይጠይቀል፡፡በመንፈሳዊ ሕይወት ስንመለከት ትላንት በተለያየ ስፍራ (ግቢ ጉባኤ ሊሆን ይችላል) ላይ ተማሪ፣ተመልካች የነበረ ዛሬ አስተማሪ፣ ምሳሌ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር በሰጠው ፀጋ ማገልገል አለበት፡፡ ለሁሉም እግዚአብሔር የሰጠው የፀጋ (መክሊት) መጠን አለ በዚያ ፀጋ (መክሊት) ለማትረፍ ግን ከፊት ይልቅ መትጋትን ይጠይቃል፡፡ ካለተረፍንበት ደግሞ እግዚአብሔር ይፈርድብናል፡፡ ለዚህ ነው ጌታችን በወንጌል እንዲያተርፉበት ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት ለሌለኛው ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡ ያተረፉበትን እያመሰገናቸው ለክብር አበቃቸው ያለተረፈበትን ባለ አንዱን ግን‹‹… አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ...›› ብሎ ወደ ፍርድ አሰናበተው፡፡ ማቴ. 2520-25 ዕብ. 314
ስለዚህ ትላንት እግዚአብሔር ፈቅዶልን ወደ ቤቱ ጠርቶን አሁን ላለንበት ጊዜ ያበቃን፣ እግዚአብሔር የሰጠን አደራ፣የገባነው ቃል ኪዳን፣የተቀበልነው የአደራ መስቀል እውነት ወደ ተግባር ቀይረነዋል ወይ? ዛሬ ዬት ነው ያለነው? ከትላንቱ ቦታ በታች ነው ወይ በላይ? ክርስትና እያደገ የሚሄድ እስከመጨረሻ መጽናትን የሚጠይቅ መንገድ እንጂ ከመሀል የሚያgርጡት አይደለም፡፡አላማዋ ለነፍስ እረፍት ማግኘት ነውና እስከመጨረሻ አጽንቶ መያዝን ይጠይቃል፡፡ (ኤር.6፡16)
ከፊት ይልቅ ለመትጋት የትላንቱን እምነታችን፣ቆራጥነታችንን ለማሰደግ በንስሀ ሕይወት መኖር፣በአምላክ ሥጋ እና ደም ዘወትር መታተም (ምስጢረ ቁርባን)፣የትምህርትና የአገልግሎት ሕይወት ማሳደግ ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን ፍርድ ይሆንብናል፡፡ የሚፈርድብን የሰማነው ቃል፣የገባነው ቃል ኪዳን፣ዘወትር ከክርስቶስ ጋር ለመኖር የተቀበልነው መስቀል … ነው፡፡ የሚያድነን ምክንያት የለምና፡፡ እግዚአብሔር ዘጋዥ በማድረግ መትጋት እና መጽናት ያስፈለገናል፡፡
ስለዚህ ያለፈውን ትጋት ማሳብ ከዚያም ከፊት ይልቅ መትጋትን መሰረት በማድረግ ወደፊት መÕዝ ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ዬት ነበርክ ሳይሆን ዬት ነው ያለኸው የሚል ጥያቄ ነው የሚጠይቀው፡፡ የትዝታ ሕይወት ትተን እውነተኛውን ሕይወት እንኑር፡፡ ለዚህም ፈጣሪ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን፡፡

No comments:

Post a Comment