ብዙ ጊዜ የምሰማው ከ1ኛ ደረጃ
አንስቶ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት የተማሪዎቻችን ውጤት ተሻሻለ ሲባል ነው፡፡ ነገር ግን ቁጥሩ ነው የጨመረው ወይ የተማሪዎች
ችሎታ? ነው ለማለት ደግሞ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተgም መጥቶ ማንበብ፣መጻፍ ሲከብደው እንመለከታለን ታዲያ ምኑ ጋር ነው የትምህርት ጥራት የተጠበቀው? አማራ ከብዛት ጥራት
ይል የለም ወይ:: ስለዚህ ተማሪዎች ምን ያህል ውጤት አምጥተዋል ብቻ ከምንል ምን ያህል አውቀዋል ምን ያህል የአመለካከት ለውጥ
አምጥተዋል ምን ያህል ተቀይረዋል ማለት ነው ያለብን፡፡ብዙ ጊዜ የተማረ ትውልድ ዘረኛ፣ጎጠኛ፣እንዳልተማረ ሲሆን፣ፍቅር የሌለው ወዘተ
ሆኖ እናገኛለን፡፡ እንዲህ አይነቱ ዉጤት፣እውቀት እና ጥበብ ተማሪ ተኮር ሳይሆን ቀርቶ ውጤት (ቁጥር) ተኮር ብቻ ሆኖ የመጣ ተማሪ
ነው፡፡እኛ የምናውቀው ትምህርት ሰውን ይለውጣል እንጂ ስያደነቁር አላየነምና፡፡ ውጤት በተለያየ መልኩ ሊገኝ ይችላልና ይህም በቡድን
ስራ፣በመኮረጅ፣በመቅዳት…፡፡ ስለዚህ በሁሉም ደረጃ ያላችሁ መምህራን ተማሪዎቻችሁ ዉጤት ተኮር ብቻ ሳይሆኑ እውቀት ተኮር እንድሆኑ
ስሩ የነገዋ የሀገራችን ተረካቢ እናናንተ ያፈራችሁት ተማሪ ነውና፡፡ ሀገራችን እንደ ቀደምቶቹ እነ ዲ/ን እንጅነር ቅጠው እጅጉ፣ዶ/ር
አክሊሉ ለማ…. ሌሎችም አይነት ሰይንትስት ለማፍራት የመምህራን ሚና ልዩ ነው፡
ትምሀርት ለለውጥ ነው እውቀት
ደግሞ የማያልቅ ጸጋ ነው
No comments:
Post a Comment