በእስከዳር ዋሲሁን
ዘመኑ የኢትዮጵያ ንጉስ አጼ ኃይለ ሥላሴ በነበሩበት ዘመን ነው፡፡ ከታማኝ ወታደሮቹ ውስጥ በንጉሡ ልዩ ቦታ የሚሰጠው
ይግዛው ገብረየስ ነው፡፡ በወቅቱ ንጉሱ ከደርግ ወታደሮች ጋር ልዩ ትግል ላይ የበሩ ጊዜ ነበር፡፡ ብዙዎች የንጉሱ ወታደሮች ንጉሱን
ክደው ለደርግ ቢወግኑም እንኳን ይግዛው ግን በለጋ እድሜው ከንጉሱ ጋር መሞትን መረጠ$ ሆኖም ግን የንጉሱ የግዛት
ዘመን ስላበቃ ንጉሱ ወደ ሞት ተሸኝተው ታማኙ ወታደር ይግዛው በልዩ ሀዘን መላ ፍለጋ ጀመረ፣ ንጉሱ እስከሞቱ ድረስ ሀገርን ለመምራት
የነበራቸው እድል ከእጃቸው ስለወደቀ ሕይወቱን የሚያተርፍበትን መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ ሚስቱ ጸንሳ ስለ ነበር
ለሷም ተጨነቀ፡፡ ሚስቱ አማከለች ሞላም የሚወለደው ወንድም ይሁን ሴት ደስተኛ የሚሆኑት ተወልደው አባታቸውን በሕይወት ሲያገኙት
ስለ ሆነ ባሏ ይግዛው የደርግ ወታደሮች እንዳይገድሉት ከሀገር እንዲወጣ መከረችሁ፡፡ ችግሩ ዬት ሀገር እንደሚሄድ ነው፡፡ ይህንን
እያሰበ ንጉሱ ከእንግሊዞች ጋር ጥሩ ቅርርብ እንዳለቸው ስላስታወሰ በእንግሊዞች እርዳታ ከሀገር ለመውጣት ወሰነ፡፡ እንግሊዞችም
በአፋጣኝ የግብዣ ደብዳቤ ከሀገራቸው አስልከውለት ይዘውት ወጡ፡፡
ይግዛው እንግሊዝ ሲደርስ የንጉሱ ታማኝ ወታደር ስለ ነበር እጅጉን ወደዱት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት እንግሊዞች በኩል
ስለ ሚሰቱ ይከታተል የነበረ ይግዛው እሱ እንግሊዝ አንደ ደረሰ ከአንድ ወር በኃላ ሚሰቱ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ ስሙንም አሸናፊ
አለችው፡፡ ይግዛውም ወደ ሀገር በቀላሉ መምጣት ስለማይችል ከኢትዮጵያ ኑሮ እንግሊዝ መኖርን መርጦ በለንደን ከተማ ኑሮውን ጀመረ፡፡
ይግዛው ለጊዜው በሀገር ውስጥ ጦር መምራትንም ሆነ ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በልምድ እንጂ የአስኳላ ትምህርት አልተማረም ነበር፡፡
ለዚህ ነበር እንግሊዞችም ይህን ሰው የወደዱት፡፡ይህ ሲሆን አሸናፊ እናቱ ገና በሕጻንነቱ ጡት ሳይጠግብ ከዚህ ዓለም በሞት ስለ
ተለየች ከአጎቱ ከገበየሁ ገብረየስ ጋር በኮልፌ ክፍለ ከታማ አደገ፡፡ ከቤተሰብ እና ከሰው ፍቅር ተለይቶ የብቸኝነት ኑሮ ይኖር
ነበር፡፡ ከዘመናት በኋላ ግን እንግሊዝ የሄደው አባቱ የእንግሊዝ ሀገር ኑሮ ሲደላው ልጁን ወደ እንግሊዝ ለመውሰድ ፈለገ ሲያማክራቸውም፣
‹‹ልጅ ካለህማ ወደዚህ ሀገር አስመጣ እኛ ሁሉን ነገር እናመቻችለታለን እናስተምረዋለን›› ብለውት በውስጣቸውም ‹‹እኛ እርጅና
ከፊቱ ድቅን ካለበት ሰው ምን እናደርጋለን ጥሩ አእምሮ ያለውን ነው፣ መቼም ካንተ የተወለደውም የተሻለ እንሚሆን እንገምታለን››
አሉ እሱ በማይሰማ መልኩ፡፡ እንግሊዞችም ሰውዬውን ስለወደዱት ስሙን ቀይረው አንቶኒ ብለው አወጡለት፡፡
ከአንድ ዓመት ቆይታ
በኋላ አሸናፊ ምድረ ኢትዮጵያን ለቆ እንግሊዝ ሀገር በረረ፡፡ እንግሊዞችም ሳይውል ሳያድር በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ የተማራትን የሕግ
ትምህርት እንዲቀጥል ወደ አሜሪካ ነጻ የትምህርት እድል እንዲያገኝ አመቻችተውለት በዮል ዩኒቨርሲቲ በሕግ ሙያ በድግሪ እና በማስተርስ
ትምህርቱን አጠናቀቀ፡፡ አሸናፊ ያልገባው ነገር ቢኖር በዮል ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው የትምህርት፣ የዩኒቨርሲቲው፣ እና የመሪዎቹ ዓላማ
ነበር፡፡ ለካ ዩኒቨርሲቲው በሰይጣን የሚያመልኩ ሰዎች ማሰልጠኛ ነው፡፡ ብዙ የፖለቲካ ሰዎች ከዚህ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡ አሸናፊም
ገና ትምህርቱን ሲማር የሚሰጠው ትምህርት ዓለምን እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል፣ ልዩ እውቀት እና ከዓለም ሰው የተሻለ እንዴት
መሆን እንደሚቻል ነበር፡፡ እሱ የማያውቀው የአምልኮ ስርዓት እንደሚፈጸምም መገመት ችሎ ነበር፡፡ ነገር ግን ትምህርቱን በተሻለ
ውጤት ስለ ጨረሰ የዩኒቨርሲቲው መሪዎች እና የአሜሪካ መንግስት የድኅንነት ድርጅት (C.I.A) አይናቸውን ጣሉበት፡፡ ይህም የአንድን
ሰው የዘር ሀረግ ማጥናት የሚቀናላቸው እንግሊዞች እና ሰይጣን አምላኪዎች አሸናፊ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ደረሱበት፡፡ የሚፈልጉትም ይህን
ነበር፡፡ ከዓለም ሀገሮች ኢትዮጵያ ልዩ ሀገር እንደ ሆነች ከኢትዮጵያውያኑ ይበልጥ እነሱ ጠንቅው ያውቃሉ፡፡ በኢትዮጵያ ልዩ ዓላማ
እና ራዕይ ስለነበራቸው አሸናፊ በመገኘቱ እጅጉን ተደሰቱ፡፡
አሸናፊ ትምህርቱን
ሲጨርስ ልዩ ቦታ ይሰጡት ጀመር፡፡ ይህም ዝና፣ ገንዘብ፣ ስልጣን ቸሩት አይቶት የማያውቀውን ነገር ሲያሳዩት እነሱ ያሉትን በሙሉ
ማድረግ ጀመረ፤ ይህም የሰይጣን ማኅበር አባል መሆን፡፡ የተሰጡት ነገሮች በልጠው ስለታዩት አባል ለመሆን ተስማምቶ ስርዓታቸው በሚያዘው
መሠረት አባልነቱን በደሙ ፈርሞ አረጋገጠላቸው፤ የ’እስከል እንደ ቦንስ’ (skull and bones) የሰይጣን ማኅበር አባልም
ሆነ፡፡ እሱ በማያውቀው ሰዎቹ በሚያውቁት ጋድርኤል የሚባል ልዩ መንፈስ አደረበት፡፡ ብዙ ስራ አሰርቶታል፣ ሰዎቹ ያሰቡትን በተለይ
ኢትዮጵያ ላይ ለሚያከናውኑት ስራ እንዲያሰራው አድርገው አሳደሩበት፤ አሸናፊ የሰይጣን ባሪያ ሆነ፡፡ አሜሪካ የምትኖር ነጻነት ተስፋዬ የምትባል አንዲት ኢትዮጵያዊት የልጁን ችግር ተረድታ ሀገሯን
እና የተለወደባትን ሀገሩን ለማየት ኢትዮጵያ ለመምጣት አማከረችሁ፡፡ እሱም ያለበት ሰይጣን ኢትዮጵያ እንዲሄድ ዓላመው ስለ ነበር
ደስ አለው፡፡ ነገር ግን ነጻነት የመንፈሱን ጠባይ ስለምታውቅ ሀገሩን ለመጎብኘት ብቻ እንደሆነ እና ሌላውን ዝርዝር ዓላማ ሳትነግረው
የረጅም ጊዜ የስራ ፈቃድ እንዲወስድ ነግራው ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት በቀጠሮ ተለያዩ፡፡ በፊትም የአሸናፊን ኢትዮጵያ መጥቶ መጎብኘት
ይፈልጉ የነበሩ የአሸናፊ አለቆች በነገሩ ደስ ብሏቸው ፈቃድ ሰጥተውት ከነጻነት ጋር በቀጠሮአቸው መሠረት ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡
አሸናፊም አጎት ሆነ
የነጻነት ቤተሰቦች ከዚህ ዓለም በሞት ስለ ተለዩ የሚያርፉበት ዘመድ ስላልነበራቸው ቆይታቸውን ያሳለፉት በተንቀሳቃሽ ድንኳን የተለያዩ
ታሪካዊ ቦታዎችን ለመጎብኘት ወሰኑ፡፡ ከእነዚህም ቦታዎች ውስጥ አሸናፊ ከያዘው ሰይጣን እንዲላቀቅ ወደ ወሰነችው ወደ አንድ ገዳም
እንዲሄዱ አግባባችው፡፡ በእሷ ሀሳብ እየተማራ ሰሜን ሸዋ ውስጥ ወደሚገኝ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ጉዞአቸውን አደረጉ፡፡ አሸናፊም
ገና ከገዳሙ ዋሻ ሲደርሱ ራሱን ሳተ የያዘው ሰይጣን ተጋለጠ መለፍለፍ ጀመረ፡፡ የመንፈሱን ምንነት እና ሀያልነት የተረዱ አንድ
በገዳም ውስጥ በልጅነት እድሜአቸው የገዳም ኑሮን የመረጡ አንድ የበቁ አባት አባ ተክለኢየሱስ የሚባሉ ባላቸው ስልጣን መንፈሱን
ተቆጣጠሩት፡፡አሸናፊ አሁን የለም እሳት ብረትን እንደሚዋሀድ ሁሉ አሁን የሚያወራው ሰይጣን፣ የሚወድቀውም፣ የሚነሳውም ሰይጣን እንጂ
አሸናፊ አይደለም፡፡ እኚህ አባትም እንደዚህ ዓይነት መንፈስ አጋጥሞአቸው ስለማያውቁ፣ በተለይ ከምድረ አሜሪካ መምጣታቸውን ጠርጥረው
ባሁኑ ጊዜ ዓለምን እየተቆጣጠራት ካለው ከ666 መንፈስ ጋር ስለተመሳሰለባቸው ብዙ ነገር ሊጠይቁት ወደዱ፡፡ እኔም በቦታው ስለ
ነበርኩ ነጻነት ይዛው ያመጣችውን ወንድም አሸናፊን ከያዘው ሰይጣን ጋር አባ ተክለ ኢየሱስ የሚደርጉትን ምልልስ በገዳሙ ስልክ መደወልም
ሆነ ጥሪ መቀበል ስለማይፈቀድ ስልኬን የበረራ ዘዴ (ፍላይት ሞድ) ላይ አድርጌ መቅዳት የተቻለኝን ደግሞ ማስተወሻዬን አውጥቼ መጻፍ
ጀመርኩ፡፡ አባ ተክለ ኢየሱስም በማደርገው ተደስተው አንዲህ አሉኝ ‹‹ልጄ እናንተ የሰይጣንን ጥብብ አታውቁም መልካም አደረግሽ!
እንዳንቺ እዚህ መጥተው ማየት ሳይችሉ ቀርተው ሰይጣን የሚጫወትባቸው ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡ አንቺም በያዝሽው መሳሪያ፣ በከተብሽው
ወረቀት ሌሎቹን ታሰተምሪያቸዋለሽ፡፡ በተለይ አሁን ወንድማችንን የያዘው መንፈስ ለየት ያለ እና ከወትሮ የተለየ እንደሆነ እገዚአብሔር
ገልጦልኛል፣ ነጩን ዓለም የሚጫወትበት አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ለማፈራረስ ማንነታችንን ሊያሳጣን የሚሰራ መንፈስ
ነው፡፡ ልጄ! እገዚአብሔር ይባርክሽ የስይጣን ባሪያ ከመሆን ፈጣሪ ያውጣሽ በርቺ›› ብለውኝ ወደ ሰይጣኑ ዙረው የያዙትን መስቀል
ግንባሩ ላይ ጭነው ጠበል ጨመሩበት፡፡ ሰይጣኑም እያጓራ ‹‹ተዋረድኩ ወይኔ! ወይኔ! እኔ ጀግናው! ተደፈርኩ! ማንም ያልደፈረኝ
ዛሬ አንተ ደፈርከኝ! በፈረንጅና በአሜሪካ እኮ እመለካለሁ እዚህ ግን ያንተ መጫወቻ ልሁን?›› እያለ ይጮህ ጀመር፡፡ አባ ተክለ
ኢየሱስም ጥያቄዎችን ተራ በተራ እያቀረቡለት ሰይጣንም መልስ እየሰጣቸው ጥያቄያቸውን ቀጠሉ፡፡
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹ለመሆኑ ስምህ ማነው እንዴተስ ያዝከው?››
ሰይጣን፡- ‹‹አንተ ደግሞ አሁን ስሜ ምን ያደርግለሃል?›› አባም በያዙት
መስቀል ሲመቱት ‹‹እሽ እሽ አታቃጥለኝ ስሜ ጋድርኤል ነው እርግጠኛ ነኝ ይህን ስም ከዚህ በፊት ከመጽሐፈ ሄኖክ ውጪ ሰው ላይ
አድሬ ሰምተኸኝ አታውቅም፡፡ ልጁን የያዝኩት ደግሞ ከዮል ዩኒቨርሲቲ ራሱ ፈልጎ መጥቶ ነው፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹ምንድነው ስራህ? ከሌሎችስ በምን ትለያለህ?››
ሰይጣን፡-‹‹እያወቅህ አትጠይቀኝ ስራዬ ብዙ ነው የመጀሪያ እናታችሁ ሔዋንን
አሳስቼ ያንን የበለስ ፍሬ እንድትበላ ያደረኳት እኮ እኔ ነኝ፡፡ አቤት ደስ ሲል! አዳም ደግሞ ጅል አይደል ሚስቱን ተከተላት ከሷ
ጋርም በላ፡፡ እኔ ከሌሎች የምለየው ሌሎች አጋንንት በሽታ፣ ምናምን ይሆናሉ፡፡ የኔ ስልጣን ግን ልዩ ነው፤ እንደ አምላካችሁ መሆን
እና ከሰው አእምሮ በላይ የሆኑ ሃጢአቶችን ማሰራት ነው፡፡ ዓለም ላይ እየተሰራ ያለውን ኃጢአት መቼም ንገረኝ እንዳትለኝ የአዳም
ልጆች በጣም የሚመቹ ናቸው ገንዘብ ካገኙ የፈለጉትን ነገር ያደርጋሉ እኔም ይህን ነው የማሳያቸው፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹እስኪ ለምን ነበር ይህን ልጅ የያዝከው? ዓላማህስ ምን ነበር?››
ሰይጣን፡- ‹‹ነገርኩህ እኮ ልጁ ራሱ ፈልጎ ነው የመጣ...ው የኛ ወደጆች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት ተማረ መጨረሻ ላይም መጥቶ በገዛ ደሙ አባልነቱን አረጋገጠልኝ፡፡ ኡፍ ወይኔ! የኔ ዓላማማ ብዙ ነበር
ምን ዋጋ አለው ያቺ ቀልቃላ የሆነች ልጅ ናት አንቀልቅላ ይዛው የመጣችው፡፡ ማምጣቷን ታምጣ እኔ ግን መች እዚህ መሰለኝ፣ ለወደ
ፊት ዓላማዬ የሆነ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ አስቀድሞ እንዲጎበኛት ነበር እንጂ፡፡ ይህ ልጅ ገንዘብ እና ስልጣን ወዳድ ስለሆነ በዚህ
ሰበብ እዚች ምድር ላይ የሰይጣን አምልኮ እንዲያስፋፍልን፣ ለምሳሌ ግብረ ሰዶም፣ መቼም ሰምተህ ይሆናል፣ ሴት ለሴት፣ ወንድ ለወንድ
እየተጋባ ነው፤ ውጪው ዓለምማ በደስታ ተቀብሎታል ስንት ጋብቻ ተፈጽሟል መሰለህ? ይህን የምናደርገው እኛ ነን በወደጆቻችን ላይ
እናድራለን፤ ጥሩ አድርገን እናሳያቸዋለን በቃ ምን ልበለህ ከዚያ ለዓለም ያስተዋውቃሉ በተለይ እያደጉ ላሉ ሀገሮች ከእነዚያ ውስጥ
ይህች ደባሪ ሀገር ኢትዮጵያ አንዷ ናት፡፡ ኡፍ ስታቃጥል፣ ስታናድድ፡፡ ልጁንም የፈለግነው ለዚህ ዓላማ ነበር፣ አሁን ምን ዋጋ
አለው ታዲያ ከሰርኩ፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡-
‹‹ሌላ ዓለም ላይ እያደረጋችሁ ያላችሁት ስራ ምንድነው?››
ሰይጣን፡- ‹‹ዓለምማ የኛው ስለሆነች ልኳን ነው የምናሳያት፡፡ የኛ ትልቁ
ጥበብ እኛ እንደሌለን አድርገን ተመሳስለን ማቅረባችን ነው፡፡ ከዚያ የምንፈልገውን ነገር እንሰራለን፡፡ የአዳም ልጆች ግን ሁሉም
ነገር በራሱ የሆነ ይመስላቸዋል፡፡ የማንገባበት ቦታ የለም፤ ሳይንስ ውስጥ እንገባለን የራሳችንን ጥበብ ለማስተማር ወይም ከፈጣሪ
ጋር የሚያጣላ እና በፈጣሪ ስራ ውስጥ ጣልቃ የሚያስገባ ትምህርት እንዲሰሙ ማድረግ፣ በፖለቲካ ውስጥ የኛ ወደጆች ብቻ ስልጣን እንዲይዙ
እናደርጋለን ከዚያ የኛን ዓላማ ያስፈጽማሉ ደም ማፍሰስና ብጥብጥ እንዲሆን፣ እምነት ውስጥ እንገባእና ደግሞ ህዝቡ ሃይማኖቱ የሚያዘውን
እንዳይፈጽም እንዲጠራጠርና በስም ብቻ እንዲመላለስ በቃ ምን ልበልህ ደነዝ ታውቃለህ? ደነዝ ሆኖ እንዲኖር ማድረግ ነው፤ ሌላው
ደግሞ በሙዚቃ እንዱስትሪ ውስጥ ገብተናል፡፡ ዘፈንም ሆነ ዘፋኝ በፈጣሪያችሁ ዘንድ የተጠላ እንደሆነ አንተም እኛም እናውቃለን፡፡
ነገር ግን የአዳም ልጆች በእምነት ሳይሆን በስሜት ብቻ ስለሚኖሩ የሚገባቸውንም የማይገባቸውንም ዘፈን ይቦንሱታል፡፡ እንዴት ወደ
ታላቅ ስልጣን እንደመጡ ሳያውቁ ቀርተው የእንግሊዘኛ ዘፈኖችን ይሰማሉ፡፡ ውስጡ ግን እኛን ነው የሚያመሰግነው፣ ስለኛ ነው የሚዘፍኑት
ዘፈኞቹ ያውቁታል፡፡ ነገር ግን አንዴ ነፍሳቸውን ለኔ ስለሸጡ ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ ሀሳባቸውን ለመቀየር አይደለም መሞከር
ማሰብ ራሱ ልዩ ቅጣት ያስከትላል፡፡ እነ ማይክል ጃክሰን ላይ ምን እንደ ደረስ ታውቃለህ፡፡ ገና እኔን ሊከዳኝ ሲያስብ ድብን! ዘፋኞቹ የሚያገኙትን ገንዘብ ብቻ በማሰብ ዘፈንን የሚከተል ትውልድ ማፍራት
ከጀመርን ቆይተናል፡፡ ታለንት ሾው እየተባለ ወጣቱን ደግሞ ያወዳድራሉ፡፡ ከሰሙ ንገራቸው በዘፈን ውስጥ እኛ ብዙ ነገር እናስተላልፋለን፡፡
ይህም ወጣቱ በዝሙት እንዲወድቅ ዘፋኞቹ እርቃናቸውን እንዲዘፍኑ ማድረግ፣ በስሜት ብቻ የሚኖር ዜጋ ካፈራን በኋላ በቀላሉ እንቆጣጠራለን
ማለት ነው፡፡ አይደለም በዚህ ዘመን ከድሮም ጀምሮ ዘፈን እናስተምር ነበር፡፡ ሀገርህ ኢትዮጵያንም መመልከት ትችላለህ፤ ዘፈን ቤት
አልበዛም? ዳንስ ቤቶች እና የማታ ክበቦችስ? ይህ ሁሉ እኮ የእኛ ስራ ነው፡፡ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ያለ ምንም ለውጥ ከዩኒቨርሲቲ
እንዲወጣ በማድረግ የነገርኩህ ቦታ ጊዜውን የሚያሳልፍ ይሆናል፡፡
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- በጧፍ ላጥ እያደረጉ‹‹ሌላ ዓለም ላይ የሚታደርገው ምን አለ?››
ሰይጣን፡- ‹‹በዓለም ላይ ሰራ ካቃለልኝ ውስጥ ዋነኛው ከዘመናት በፊት ጀምሮ
የነበረ እና የተቋቋመው የምሥጢር ማኅበር የሚባል ደርጅት ነው፡፡ የዚህ ድርጅት ዓላማው ሰፊ ነው፡፡ የማይገባበት ቦታ የለም ትልቁ
ስራዬን የሚሰራው ይህ ማኅበር ነው፡፡ የተለያዩ ሰላማዊ የሚመስሉ ማኅበራትን ያቋቁምና በዓለም ደረጃ፣ በአህጉር ደረጃ ከቻለም በሀገር
ደረጃ ዓላማችንን ያስፈጽማል፡፡ የአዳም ልጆች ደግሞ ጅሎች አይደሉ! መከተል ብቻ ነው፡፡ የዚህ ማኅበር መሪዎች ከኔ ጋር ልዩ ግንኙነት
ያደርጋሉ፣ የፈለጉትን ጥበብ ሁሉ እሰጣችኋለሁ፡፡ ይህ ልጅ ራሱ ከምስጢር ማኅበራቱ አንዱ ውስጥ ነው የሚሰራው፡፡ እባክህ አታሰቃየኝ
አሁን ይበቃኛል››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- አባም በመገረም ‹‹የምስጢር ማኅበር የምትለው ደግሞ መች ነው የተቋቋመው?
ስራውስ ምንድነው?››
ሰይጣን፡ ‹‹አንተ መቼም ለህዝቡ ለማሳወቅ ነው እንጂ ለራስህ እንዳልሆነ
ይገባኛል ይህን ማዋቅ የፈለከው፣ ይሁን አንዴ ተይዣለውና እነግርሃለሁ፡፡ የሰይጣን ማኅበራት ከተቋቋሙማ ቆይተዋል ደግሞም ብዙ ናቸው
አላማቸው ግን አንድ ነው፡፡ ይህም አድስ በኛ የሚመራ የዓለም አስተዳደር፣ መንግስት፣ እምነት፣ባህል እና ቋንቋ ማምጣት ነው፡፡
እናም የምስጢር ማኅበራት መስራቾች በዓለም ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ናቸው፣ አባል የሚሆኑትም ዓለም የሚሰግድላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ለምሳሌ ሀጋራችሁ ሳትቀር የምትወደው ባረክ ሁሴን ኦባማ፣ ቡሽ እና ቤተሰቦቹም ጭምር አባል ናቸው፡፡ መቼም ለማመን ይከብድሃል ብዬ
አምናለው፡፡ እንደ ምሳሌ የጠቀስኩልህን ሰዎች ታቃቸዋለህ ምንም እንኳን የዘመኑን ቴልቨዢን እና ሬዲየ ባትከታተልም እግዚአብሔር
በዓለም ውስጥ የሚደረገውንና የወደፊቱን እንደ ገለጠልህ አውቃለሁ››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ስለ እሳቸው ሲያወራ ስላልተመቻቸው፣ በያዙት በትረ መስቀል ወግተውት
‹‹ስለ ራሴ መች ጠየኩህ? የምስጢር ማኅበራቱ እየሰሩ ያሉት ምንድ ነው? አልኩህ እንጅ፡፡››
ሰይጣን፡- ‹‹ወይኔ እንዲህ ልዋረድ! በቃ ቶሎ ልንገርህ እና ሸኘኝ የምስጢር
ማህበራት ዋና ስራቸው እኛን ማምለክ፣ ለኛ መገዛት፣ እኛ በምንለው መንገድ መሄድ፣ በኛ የሚመራውን አድሱን የዓለም አስተዳደር ማምጣት
ነው፡፡ ለዚህ ሲሉ በዓለም ያለው የህዝብ ቁጥር በየ ጊዜው እንድቀንስ ይደረጋል፤ ያልታሰቡ ጦርነቶች በመፍጠር፣ ድንገተኛ አደጋዎች፣
የቦምብ ፍንዳታ፣ በላቦራቶሪ ውስጥ በሚፈጠሩ ቫይረሶች (በሽታዎች)፣ የሚገርመው ባሁኑ ጊዜ ዓለም የተስማማበት የወሊድ መቆጣጠሪያ
መንገዶች ምንም አንኳን በወዳጆቻችን ቢሰሩም በሙሉ የኛ ስራ ናቸው፡፡ ሌላው ስራቸው ይህች ዓለም አንድም ቀን በሰላም እንድታድር
አይፈልጉም፡፡ ምክንያቱም ሰላም ሲጠፋ ራሳቸው በፈጠሩት ሁከት ራሳቸው ደግሞ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ይጠራሉ፣ ራሳቸው ይወስናሉ ዓለም
በአንድ መንግሥት ልትተዳደር ይገባል ብለው፡፡ መቼም ይገበሃል ዓለም አንድ መንግስት ከሆነች አንድ ሃይማኖት እሱም የሰይጣን እምነት፣
አንድ ባህል ይህም ባሁኑ ጊዜ የራሳችሁን ባህል ነው እንዴ የምትከተሉት? የምእራብ ባህል አይደል እንዴ? ይህማ ተሳካልን! ደስ
ሲል! ግን ምን ዋጋ አለው እየታገለጥን ነው፡፡ ብዙ ሰው ነቅቶብናል፣ አብዛኛው ህዝብ ግን ደንዝዟል፡፡ የብዙዎች አእምሮ በዘፈን፣
በተለያዩ ፊልሞች፣ በሚተላለፉ የስፖርት ፕሮግራሞች በቃ! ብዙ ናቸው የሰውን አእምሮ የተቆጣጠርንበት፤ ለምስጢር ማኅበራቱ እኛ የተወሰነ
ነገር እናሳያቸዋለን የከባዳቸውን ደግሞ ፊት ለፊት ጠርተውን ይጠይቁናል፣ እኛም ለወደጆቻችን ቅርብ ስለሆን በጠሩን ጊዜ እንመጣላቸዋለን
የፈለጉትን ነገር እንነግራቸዋለን ከፈለግንም እኛም እንሳተፋለን በተለይ የሰው ደም ማፍሰስ ላይ ፍርዱን ከቻልን ቀዳሚዎች ነን፡፡ይህን
ስናደርግ አምላካችሁ ዝም አይልም ብዙ እቅዶቻችንን አፍርሶብናል ይህ ባይሆንማ በዚህ ዓለም ያለው የአዳም ልጅ ወይ ባለቀ ወይም
በተገዛልን ነበር፡፡ አንተ ራስህ ወጣ ብለህ የዓልምን ነገር ብትመለከት ህዝቡ በቃ ማንነቱን ጥሎ ሌላ መስሏል የሚለብሰው የልብስ
ዓይነት፣ አነጋገሩ፣ አኗኗሩ በቃ ምን ልበልህ ሁሉ ነገሩ ተቀይሯል፡፡ የራሱን ማንነትማ ከረሳ ቆየ በሙስና ዓለም ተዘፍቆ የራሱን
ጥቅም እንጂ የሀገር፣ የወገን ኑሮ አያስጨቀውም፡፡ ይህን ያደረግነው ደግመ እኛ ነን፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- በያዙት
ጧፍ ላጥ እያደረጉ ‹‹ተናገር! አጭበርባሪ! ከዚህ ውጪ ዓለም ላይ ያደረጋችሁት ነገር ምነ አለ?››
ሰይጣን፡- ‹‹ዋና ዋናውን እኮ ነግሬሃለሁ! ይሁን ካልክ እነግርሃለሁ እኔ
ነኝ እያወኩ ወደዚህ ሀገር የመጣሁት፡፡ ኡፍ! በቃ አይመችም ለኑሮ ፈረንጅ ይሻላል፤ ፈረንጅ ጣጣ የለውም በዚህ ምድር እስካለ ከደላው
ከሞት በኋላ ያለው ሕይወት አይጨንቀውም እንደ ፈለግን ይሆንልናል፤ ባሁኑ ጊዜ አበሻውም በፍጥነት ወደኛ እየመጣ ቢሆንም፡፡ሌላ ዓለም
ላይ ያደረግነው ነገር ቢኖር በዓለም ያለው ሕዝብ ሰላም እንዳያገኝ ማድረግ፣ በዘር፣ በጎሳ መከፋፈል፣ ሁል ጊዜ ጦር እና የጦርነት
ወሬ እንዲሰማ ማድረግ፤ ከዚያ ተስፋ ቆርጦ ወደኛ ይመጣል፡፡››
አባ ተክለ ኢሱስ፡- ‹‹ይህን ደግሞ አንዴት ነው የምታደርገው?››
ሰይጣን፡- ‹‹አውቀህ እኮ ነው የምትጠይቀኝ! ምን አይነት ጨቅጫቃ ነው ባካችሁ
ኡፍ! እሽ እነግርሃለሁ፡፡ ሰላም ማሳጣት ያልኩህ እኛ እና ወደጆቻችን በፈጠርናቸው የስለላ ድርጅቶች፣ የፀረ አሸባሪዎች ቡድን ተጠቅመን
ህዝቡ በማይጠረጥር መልኩ አደጋ እናደርሳለን፣ ሕዝቡ ይሞታል፣ ሰላም ያጣል፡፡ እስኪ ከዓለም ጦርነት ጠፍቶ ያውቃል? አሁንማ ጦርነትን
ስራቸው ያደረጉ እስኪመስል ድረስ ሁል ጊዜ ጦርነት ነው፡፡በዚህ ጊዜ ደስ ይለናል፤ ደም ሲፈስ፣ ሰው ሰላም ሲያጣ፣ ሲሰደድ፣ ሲረበሽ
በቃ ምን ልበልህ እኔ የክፋትና የሀሰት አባት አይደለሁም! ክፋት በምድር ሲደረግ ደስታውን አልችለውም ልክ አምላካችሁ መልካም ሲደረግ
እንደሚደሰት ሁሉ እኔም እደሰታለሁ፡፡ ኡፍ! ምን አይነት ስቃይ ነው? አንዴ ተፈርዶብኝ የለ! ሳወራ እሳቱም ስለሚበርድልኝ ልንገርህ፡፡
በዓለም ከጥንት ጀምሮ ስንሰራ የነበረው አንድ የሆኑትን የአዳምን ልጆች በዘር፣ በጎሳ እንዲከፋፈሉ ማድረግ ነው፡፡ በዚህማ የተሳካልን
በዚህች ልዩ በሆነች በሀገራችሁ ነው፡፡ በሌላ ዓለም ያሉ ብዙም ልዩነት የላቸውም ቢበዛ በጎሳ ነው የተከፋፈሉት ኢትዮጵያ ግን በብሔር
እና በጎሳ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ይህችን ሀገር ልዩ ያደርጋታል፡፡ መቼም መጽሐፍ ታውቅ የለ? ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን
ምና ምን... ተብሎ ተጽፎ የለ? ዛሬ ግን ያ የለም፤ አማራው ከኦሮሞ ጋር፣ ትግሬው ከአማራ ጋር ሌላውም ከ80 በላይ የሚሆኑ ብሔር
ብሔረሰቦች አብሮ መኖር ከብዳችኋል፡፡ ገና ሲገናኙ አንድ ሀገር ውስጥ ሆነው ከዬት ሀገር ነው የመጣኸው ይባባሉ የለ? ድሮ እኮ
እንዲህ አልነበረም አማራው ከኦሮሞ ጋር፣ ትግሬው ከአማራ እና ከኦሮሞ ጋር፣ ኦሮሞው ከጉራጌ እና ከወላይታ ጋር ተጋብቶ ይኖር የነበረው
አንድነት አሁን የለም፡፡ አቤት ሲመች! በቃ ሸኘኝ ባክህ አታስለፍልፈኝ››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹ቆይ መሄዲህ ዬት ይቀራል›› አሉና በጠበል እያቾፉ ‹‹ሰውን በዘር
መከፋፈል ለምን ይጠቅመሀል?›› አሉ፡፡
ሰይጣን፡- ‹‹ሞኝ ነህ እንዴ! ሰውኮ በዘር በቋንቋና በጎሳ ከተከፋፈለ በቃ
ለኛ ተማረከ ማለት እኮ ነው፡፡ አምላካችሁ ይህን ይጠላ የለ? እኛ ደግሞ ይህን እንወደዋለን፤ በቀላሉ ስራዎችን ለመስራት ያስችላል፡፡መቼም
መጽሐፍ ቅዱስ አላስተምርህም መለያየት ካለ እኮ የእግዚአብሔር መንግስት መውረስ አይቻልም፡፡ ለገነት ወይም ለመንግስተ ሰማያት ካልሆነ
ደግሞ ለኛ ነው ማለት ነው ይህን አይደል እንዴ ታዲያ የምንፈልገው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችሁንም ያገኘናት በዚህ በኩል ነው፤ እስኪ
ተመልከት በፖለቲካ መድረክም፣ በትምህርት ቤትም፣ በተለያዩ የዓለማዊ ስራ ቦታዎችም፣ በቤተ እምነቶችም ለመሆኑ ዘረኝነት የሌለበት
ቦታ አለ ብለህ ታምናለህ? አሁን ያለው ትውልድ ዘረኛ ቢሆንም ቤተሰቦቻቸው ግን ዘረኞች አልነበሩም፡፡ ይህች ሀገርም እዚህ የደረሰችው
በዚያ ፍቅር ነው እንጂ አሁን ባላችሁማ ገና የባሰ እየጠፋች፣ በእርስበርስ ጥላቻ ሲወጋገዙ ገና ከዓለም መጨረሻ ያደርጓታል፡፡ አምላካችሁም
ዝም ያለው ለዚህ አይደል እንዴ? ከዚያ የራሳቸው ጥፋት አይታያቸውም በድኅነቷ ብቻ ይጠሏታል፤ ሌላ ሀገር እና ዓለም ይናፍቃቸዋል፡፡
አንድ ቢሆኑ ግን ለኛም እሳት ትሆናለች ከአምላካችሁም መልስ ባገኛችሁ ነበር፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹መንግሥት አላችሁ አይደል?እስኪ አወቃቀሩን ንገረኝ››
ሰይጣን፡- ‹‹የኛ መንግስት ፍጹም አይደለም እንጂ ጠንካራ ነው፡፡ ዓላማውን
በትክክል ከግብ የሚያደርስ የመንግሰት ስርዓት አለን፡፡ መቼም በትዕቢታችን ከሰማይ ከወደቅን ጊዜ ጀምሮ አለቃችን ሳጥናኤል ሶስት
እጅ ነው ይዞ የወረደው እኔንም ጨምሮ ማለት ነው፡፡ ይዞን እንደ ወረደ መንግስቱን ከሲዖል እስከዚች ምድር ዘረጋ፤ እሱ የበላይ
ሆኖ እኛን በስሩ አደረገን፡፡ ከዚያም ነፍሳትን ወደ ሲዖል የምናግዝበት መንገድ ሁሉ አዘጋጀልን፡፡ስማኝ በቃ ልንገርህ ሶስት እጅ
ከሳጥናኤል ጋር ወድቋል ብየሃለሁ የመጀመሪያው ሳጥናኤል ፈጣሪ ነው ብለን የሰገድንለት፣ ሁለተኛው የተጠራጠሩ እና ሶስተኛው ነገሩን
ሳይመራመሩ ቀርተው ዝም ያሉ ነበሩ፡፡ ለሶስቱም የራሳቸው ግዛት አላቸው፡፡ በሳጥናኤል ያመኑ ሲዖል የተጣሉ እና በባሕርያቸው በጣም
ክፉዎች የሆኑ ኃያላን ናቸው፣ የተጠራጠሩ የምድር አጋንንት ሆነዋል እነዚህ ደግሞ ሰውን የማሳት ሥልጣን ባይኖራቸውም ደዌ ወይም
በሽታ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ሰይጣን ለከፈኝ፣ መጋኛ መታኝ ምና ምን ሲባል አልሰማህም? ይህንን የሚያደርጉት በምድር ያሉ
ሰራዊቶቻችን ናቸው፡፡ የመጨረሻው ደግሞ ዝም ያለው የሰይጣን ቡድን
ነው፡፡ አምላካችሁ እንዚህን አየር ላይ ነበር የበተናቸው የአየር ጋኔንም ተባሉ፤ ስራቸው የሰው ነፍስ ከሰው ተለይታ ስትወጣ ማስጨነቅ፣
በምች እና በዓይነ ጥላ ማፍዘዝ ነው፡፡ እንዲሁም ሌሊት ከሶስት ሰዓት ጀምረው ለፍጥረታት በሽታ የሚሆነውን መርዝ ከቤት ጀምረው
እስከ ውጪ ባለው የባሕር ውኃ ድረስ ይረጫሉ፡፡ ያን የጠጣ ሰው የሆድ በሽታ ይይዘዋል፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ያን ጊዜ ተዋግቶ
ከሰማይ የጣለን ሚካኤል የተባለው መልአክ ሌሊት ሰባት ሰዓት መጥቶ ባርኮ ነጻ ያደርገዋል፡፡ ልክ ስምንት ሰዓት ሲሆን ሚካኤል በዓለም
የሚገኘውን ውኃ ባርኮ ወደ ሰማይ ሲያርግ ዶሮ እሱን እያየ ይጮኻል፤ ዶሮ መጮኹ ውኃው ተባርኳል ማለቱ ነው፡፡ የአዳም ልጆች ግን
ሰዓቱን እንጂ ምክንያቱ አይገባቸውም፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹ታዲያ ሶስታችሁ አንድ ናችሁ ወይስ ትለያያላችሁ?››
ሰይጣን፡- ‹‹አንተ ደግሞ ሞኝ ነህ ልበል! ልዩነታችን የቦታችን መለያየት ነው፡፡
ዓላማችን ወይም አንድነታችን ግን ነፍሳትን በተለያየ መንገድ ወደ ሲዖል ማጋዝ ነው፡፡እነዚህ ሶስቱ መንግስታት የተለያየ ዓላማ ያለቸው
አስመስለን እናሳያለን ሆኖም ግን ዓላማቸው አንድ ነው፤ መቼም ሰይጣን ነን ብለን ወደ እናንተ አንመጣም ማን ያቀርበለናል ሳይንስን
እንጂ ፈጣሪን ከማይከተሉ ከፈረንጆች በቀር፡፡ ››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹እሺ አሁን ባሁኑ ጊዜ የተለያየ የሕብረተሰብ ክፍልን እንዴት ነው
የምትቆጣጠረው እና የምትፈትነው?››
ሰይጣን፡- ‹‹እባክህ ተወኝ! ሸኘኝ ይበቃኛል! አሰቃይተኸኝ ምን ታገኛለህ?
ሁሉ ነገር ተቀይሯል የሰው ጠባይ ብትል የዓለም ሁኔታዋ፡፡ ወጣቱን እስኪ ተመልከት ለዘፈን የተገዛ ሆኗል፣ ለሀገር ውስጥም ሆነ
ለውጭ ሀገር ዘፈን፤ ዘፋኞችን የሚያመልክ በቃ ምን ልበልህ ማንነቱን አጥቷል፣ የራሱን ባህል ትቶ የውጭ ሀገር ባህል የሚከተል፣
አለባበሱን፣ አነጋገሩን፣ አኗኗሩን ተመልከት በአካል እዚህ ሆኖ በመንፈስ ግን አሜሪካ እና አውሮፓ ይኖራል፡፡ ለዚህ እኮ ነው ስለ
ሀገር ጉዳይ የማይገባው፡፡ እስኪ ሌላውን ነገር ደግሞ ልንገርህ መቼም አንዴ ተይዣለሁና፡፡ ባሁኑ ጊዜ ያለውን የኃጢአት ብዛት፤
ዝሙት፣ መገዳደልና ለተለያየ ሱስ መገዛት ለምሳሌ ጫት፣ ሲጋራ፣ ሺሻ እና መጠጥ ናቸው፡፡ በቃ እንዴት አድርጌ ልንገርህ ኃጢአቱ
ኃጢአት እንዳይመስል አድርገን ነው የምናሰራው ለዚህ ነው ሰዎች አእምሮኣቸው ሲደነዝዝ ኃጢአት የሆነውን ነገር ሕጋዊ እናድርግ የሚሉበት
ዘመን ላይ የደረስነው፡፡ የሚገርመው ግን ሁሉም ነገር በኛ መከናወኑ ነው፤ እነሱ መሳሪያ ናቸው፡፡ እስኪ ተመልከት ድሮ ክብር የነበረ
የድንግልና ሕይወት አልረከሰም? ዛሬ ድንልናውን ጠብቆ የሚኖር ሰው ፋራ ይባላል፤ በድብቅ ይቃም የነበረ ጫት፣ በስውር ይማግ የነበረ
ሲጋራ ባሁኑ ጊዜ በአደባባይ አይደል እንዴ፡፡ የወጣቱን አለባበስ ደግሞ ተመልከት የኔ እኮ ነው፡፡ የሴቶችን አለባበስማ ተወው ይመቻል፤
ፈጣሪ የሚያዝንበት እኔ ግን አእምሮአቸውን ስለ ተቆጣጠርኩ ደስታዬ ወደር የለውም፡፡ ሌላው ወጣቱን ክፍል የያዝኩት በፊልም እንዱስትሪ
ነው፤ የወጣቱን አእምሮ የሚያደነዝዝ እንዲሰሩ ወደጆቼን እመክራቸዋለሁ እነሱም አሳምረው ያቀርቡለታል ወጣቱም እድሜ ልኩን አንድም
ቀን እውነተኛ ኑሮ ሳይኖር የፊልም ኑሮ እየኖረ ያሳልፋል፡፡ በዚህ አእምሮው እኛ ከምንሰጠው ውጪ ሌላ ነገር አይቀበልም ትምህርት
ብትል ምክር ምናምን አይሰማህም፡፡ አንተ የድሮውን ነው የምታስበው ባሁኑ ጊዜ እኮ ተማሪው ከትምህርት ይልቅ ቪዲዮ ጌም መጫወትን፣
እንተርኔት ላይ መጣድን፣ ፊልም እያየ መዋልን እና በፈረንጅ የሚደረገውን የስፖርት ትዕይንት መመለከትን የሚመርጥ ሆኗል፡፡ እስኪአንድ
ጥያቄ ልጠይቅህ ያ የሀገራችሁ ልጅ ማነው አሜሪካን በስነ ፈለግ ጥናት ከፍ ያደረጋት? ኧረ ስሙ ሊጠፋኝ ነው እንዴ? ያ ማነው ቂጣው
ነው ቅጠው እጅጉ የምትሉት እሱ እኮ ከዚህች ሀገር የወጣ ሳይንቲስት
ነው ለነገሩ እናንተ ምን እንደ ሰራ ዬት ታውቃላችሁ፡፡ ዛሬ በብሔራዊ ስነ ፈለግ እና ሕዋ አስተዳደር (NASA) የተለቀቁ
መንኩራከሮች ወሳኞቹ በሱ የተፈለሰፉ ናቸው፤ ለዚህ እኮ ነው በምድረ አሜሪካ በዚህ ድርጅት ውስጥ በሱ ምክንያት ኢትዮጵያውያን የሚከበሩት፡፡
ዛሬ ያለውን ኢትዮጵያዊ ደግሞ መመልከት ትችላለህ፤ ፈረንጅ በሚሰራው ቴክኖሎጂ መዝናናት እና መተበት እንጂ አንድም ቀን እኔ ለምን
አልሰራውም ብሎ አስቦ አያውቅም፤ በኛ አእምሮው ቁጥጥር ስር ሆኗላ፣ ፌስ ቡክ የሚባል ነገር አለ ብዙ የተዘናጋበት፤ ወጣቱ እሱ
ላይ ያፈጣል እንጂ መች ይመራመራል! ትምህርቱ እንደሆነ ውጭ በፈረንጅ ምድር የሚሰጠው ራሱ እዚህ ሀገር የሚሰጠው ነው፡፡ ግን ወጣቱ
ለፈተና እና ለስም እንጂ ለለውጥ አይማርም፡፡ እንጅነር መባልን እንጂ የእንጅነር ስራ መስራት አይፈልግም ምን ልበልህ ወጣቱ እድሜውን
ምንም ሳይሰራበት እንዲጨርስ በማድረግ መጨረሻ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ከዚያም ወደአልተፈለጉ ተግባራት እንዲገባ በቃ ኡፍ! አታስጨንቀኝ!
አትጨቅጭቀኝ! ከዚያማ... ወደ መጠጥ፣ ወደ ዝሙት፣ ወደ ጫት፣ ወደ ሲጋራና በሙስና ዓለም ውስጥ ይዘፈቃል፡፡ ባጠቃላይ መልካም
ነገር ሁሉ ያስጠለዋል፡፡ከዚያም ባልኩህ ሱሶች እና ክፉ ተግባራት ላይ እየተሰማራ አእምሮውን ስቶ ጎዳና ላይ የሚወደቅ፣ ቱቦ ውስጥ
የሚያድር፣ ለተለያየ በሽታ የተጋለጠ ይሆናል፡፡እባክህ ተወኝ! ከዚህ የሚበልጥ ደስታ አለ እንዴ? የሚገርመው ደግሞ እነዚህ የወደቁ
ሰዎችን ብቻ አይደለም የምንቆጣጠረው፣ ተመልካቹንም ነው እንጂ፡፡ መንገድ ላይ የወደቀውን እያዩ እና እየጠሉ እንዲያልፉ፣ በጫት
ስፍራ የሚንከራተተውን አበሻም! ሲያስጠላ! ሲከረፋ! አቤት ሲሸት! እያሉ እንዲያልፉ በማድረግ፣ መጠጥ ቤት መኖሪያ ያደረገውን ሲመለከቱ
ደግሞ ይህ ጋን! የአልኮል ፋብሪካ! እያሉ እንዲፈርዱ በማድረግ አእምሮአቸውን እንቆጣጠራለን፡፡ ምክንያቱም የኛ ጥበብ አንድ ሰው
በሆነ ነገር ከጣልን ሌለው ደግሞ በሱ ምክንያት እንዲወድቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ እንዲያስብ ማድረግ ነው፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹ለመሆኑ አሁን የያዝከውንም ሆነ የተቆጣጠርከውን ትውልድ አሰቃይተህ
ምን ታገኛለህ? መጨረሸህስ ምንድነው?››
ሰይጣን፡- ‹‹ፈጣሪያችሁ በሰው መልካም ስራ ይደሰት የለ? እኔም ደግሞ ሰው ክፉ
ሲሰራና ያሰበው አልሳካለት ሲል ደስታውን አልችለውም፡፡ መጨረሻዬንማ አውቀዋለሁ ተከታዬቼ ግን አያውቁም ለዘላለም የሚኖሩ ይመሰላችኋል፡፡
ለዚህ አይደል እንዴ አሜሪካ ውስጥ በሳንፍራንሲስኮ ውስጥ ቤተ መቅደስ ሰርተውልኝ የሚየመልኩኝ፡፡ ደስ የሚለው ደግሞ ይህን አምልኮ
በዓለም ላይ ሁሉ ለማሰራጨት ዓላማ አለኝ፡፡ በተለይ ይህን ልጅ የያዝነው በሀገራችሁ ይህን ተግባራዊ እንዲያደርግ ነበር፤ ቢሆንም
ከዚህ በፊት በተለያዩ ሰዎች ገብተናል ምልክቶቻችንን በተለያየ ቦታ አስቀምጠናል፡፡ ኡፍ! ተቃጠልኩ! መጨረሻዬም ከወዳጆቼ ጋር ለዘላለም
ወደማይጠፋ እሳት መጣል ነው፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን በትጋት እሰራለሁ፡፡ ሌላ ስራ የለኝማ በቃ ሸነኝ አታሰቃየኝ ምን አይነት መነኩሴ
ነው ባካችሁ! አይበቃህም? ይህን መረጃ እኮ ለዓለም አናሳውቅም ለመስጠትም አስበን አናውቅም ዛሬ ግን ፈጣሪያችሁ ልጁን ይዛ የመጣችውን
ይህችን ቀልቃላ ልጅ አጋጥሞን፣ ባንተ ላይ ያለው የፈጣሪ መንፈስ ይዞኝ አዋረደኝ፡፡››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹እሽ
አሁን መሄድ አትፈልግም?››
ሰይጣን፡- ‹‹ኧረ እሄዳለሁ! እስካሁንም በራሴ ፈቃድ አይደለም አንተ ነህ ይህን
ሁሉ ሰዓት ያቆየኸኝ በቃ እባክህ ሸኘኝ ወደ ቦታዬ ይሻለኛል›› አለ መሬት ላይ እየተንፈራፈረ፡፡
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹ዬት ነው የምትሄደው?››
ሰይጣን፡- ‹‹ይህንንም አታውቅም? ቦታዬማ ሲዖል ነዋ! ደግሞ ሌላ ትእዛዝ
ከአለቃዬ እስኪሰጠኝ ድረስ ትንሽ ሄጄ ልቃጠል፤ የትም ብሄድ፣ መጨረሻዬም መቃጠል አይደል! ሰው ላይ ሲሆን ግን አርፋለሁ፡፡ አሁን
ባንተ ዙሪያ ያለው ህዝብ እና በዓለም ያለው ሕዝብ እኮ ጤነኛ ይመስለዋል፡፡ ነገር ግን የኛ ሰራዊት ተመሳስሎ ከእሱ ጋር ይኖራል፤
ይህ ነው ሕዝቡን ያዘናጋው፡፡ ሁሉም ወደ ፈጣሪ ቢመለስ ይድናል፡፡ ኧረ ባክህ! ባክህ! ተወኝ ሊሂድበት ሸኘኝ ከዚህ እዚያው ቦታዬ
ይሻለኛል$››
አባ ተክለ ኢየሱስ፡- ‹‹እሽ አሁን በፈጣሪ ስም የልጁን ልብ መልስ! ሰባት ጊዜ ጩኸህ ወደ
ሲዖል ሂድ! ዳግም ብትመለስበት የፈጣሪ የመለኮት እሳቱ ለዘለዓለም ያንዲድህ፣ የሰማይ ሰራዊት ዘወትር ይቀጥቅጡህ››
እሱም እያጓራ ሰባት
ጊዜ ጮሆ ልጁን ለቆት ሄደ፡፡ እኔም ሳላስበው ጉነጮቼ በእንባ ታጥበዋል፡፡ እስከዛሬ የማላውቀው ጉድ በዓለም ላይ መሰራቱ እና የአሸናፊ
ሕይወት አሳዘነኝ፡፡ አሸናፊም ወደ ራሱ ተመልሶ ወደ ገዳሙ መምጣቱን ማስታወስ ጀመረ፡፡ ወደ ኋላ ዞር ሲል ረጅም የመነኮሳት ልብስ
የለበሱ ከፊታቸው በቀር ሌላ ሰውነታቸው የማይታይ አባ ተክለ ኢየሱስን ተመለከተና በእጃቸው ያለውን መስቀል ተሳለመ፡፡ አባም
‹‹ልጄ ለዘመናት ያሰረህ ሰይጣን ወቶልሃል ፈጣሪህን አመስግን! ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ራስህን ጠብቅ፣ በሰላም ሂድ›› አሉት፡፡
እሱም ከአባ አሻግሮ ሲመለከት ፊት ለፊት ብዙ በገዳም ያሉ አባቶች፣ እኔ እና ይዛው የመጣችሁን ነጻነትን ተመለከተ፡፡ ሌሎችን ስላላወቀ እንባ እየተናነቀው ሄዶ ነጻነት ላይ ተጠመጠመባት
‹‹ፈጣሪ ይስጥሽ ነጻነት፤ እስከዛሬ መች አወኩ! ለካ ይህ ነበር ሲያሰቃየኝ የነበረው? ነጻነት! የሆነውን ነገር በሙሉ ስንሄድ
ትነግሪኛለሽ›› እያለ ነጻነት የሚለብሰውን ጋቢ ሰጥታው ፈቀቅ ብለው አንድ ድንጋይ ላይ ተቀመጡ፡፡ እዚያ ያለው ሕዝብም ግማሹ እያለቀሰ፣
ሌላው ደግሞ እየተገረመ፣ አንዳንዶች ወጣቶች ደግሞ እርስ በርስ ‹‹አንተ ሰይጣን እንደዚህ የሚሰራ አይመስለኝም ነበር ለካ የፊልም፣
የፌስቡክ፣ የቪዲዮ ጌም ሱስ ያስያዘኝ ለካ ይህ አጋንንት ነው አንዴ? እስከዛሬ ተሸውጃለሁ ፈጣሪ ብቻ ይርዳኝ›› አለ አንዱ ከመካከላቸው፡፡
ሌሎችም በአንድነት ሳይደማመጡ ‹‹ኧረ እኔ ራሴ ብዙ የምተወው ነገር አለኝ በስንት ነገር ተሸውደናል ባካችሁ›› እያሉ ሲያወሩ ሌላውም
ወደየግል ወሬ ሲያመራ አባ ‹‹በቃ ይብቃችሁ! ስንነግራችሁ ያልሰማችሁትን፣ በየ ቦታው ትምህርት ሲሰጥ ያላስተዋላችሁትን ዛሬ ግን
በተግባር አያችሁት፣ ሰማችሁት ከዚህ የሚበልጥ ትምህርት አልሰጣችሁም፡፡ ልጆቼ ራሳችሁን ጠብቁ፣ ዘመኑ ክፉ ነው፤ ወጣቱ፣ ሕጻናቱ
ሽማግሌው ሳይቀር ቅድም ሲነገር በነበረው ነገር ተይዞ ባሪያ ሆኗል፣ በጊዜው መስራት ያለበትን ሳይሰራ እድሜውን በከንቱ እያሳለፈ
ነው፣ ለረሳችንና ለመጭው ትውልድ እናስብ የምናወርሰው ነገር ምንድን ነው? ተጠንቀቁ ሰይጣን ጥበበኛ ነው፤ እኛ ትላንት ነው ወደዚህ
ምድር የመጣነው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥም ከዚህ ዓለም በሞት እንሄዳለን ሰይጣን ግን ሰባት ሺህ ዓመት ከመንፈቅ የስራ ልምድ አለው፡፡
ሰውን እንዴት እንደሚጥልና እንደሚያጠፋ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በተለይ በዓለም ላይ ያለውን ነገር በሙሉ ደስ ስላላችሁ ብቻ አትውደዱ
መርምሩ፤ ‹‹በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል››፡፡ ዓለምም እንዲሁ ናት፡፡ ሁሉ ነገሯ ይጣፍጣል ሳትቆይ ግን በጸጸት
ትገድለናለች፣ ተስፋ ታስቆርጣለች፡፡ ተስፋ የቆረጠ ሰው ደግሞ መልካም ነገር አይሰራም፡፡ ነገሮችን ሁሉ መርምሩ ከአባቶች አትራቁ፣
አውቀናል ብላችሁ በዚህ ዓለም ዕውቀት አትመጻደቁ፣ ያልተማሩ ብላችሁ የምታስቧቸው አባቶቻችሁን ስሙ ትክክለኛ መንገድ በእነሱ እጅ
ናት፡፡ ዘመን ያመጣውን በሙሉ አትቀበሉ፡፡ በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን የጎደለን የለም፡፡ በታሪክ ብንል የመጀመሪያዎች፣ በስነ ጽሑፍ
ቢባል የመጀመሪያዎቹ ለዚያውም በራሳችን ፊደል እና ቋንቋ፣ በስነ ሕንጻ ቢባል ቀዳሚዎች ነን፤ ሌላ ሀገር የሌሉት እነ አክሱም፣
እነ ላሊበላ፣ እነ ጀጎል እና ሌሎች እኮ የኛ ናቸው፡፡ ዛሬ ግን የራሳችንን ትተን ባዕዱን ስለናፈቅን ያን ጊዜ የነበረ፣ ጥብብ
ከእኛ እጅ ለሌላ ተላልፋ ተሰጠች፡፡ የራሳችሁን አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ ከእናነት የተሻለ መስሎ የሚታያችሁ ነገር
የእናንተን ለማስጣል እንጂ ከእናንተ በልጦ አይደለም፡፡ሁል ጊዜ የሚያሳዝነኝ የ80 ብሔር ብሔር ሰብ የሖነች ሀገር እንዴት 81ኛ
ፍለጋ ወደ ውጭ ትሄዳለች? ይህን ራሱ መች ጠገብን? ይህ እኮ ውበታችን ነው እኛ ግን ዛሬ አባቶቻችን ያቆዩልንን አንድነት ዛሬ
በታተነው አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ትግሬ ወዘተ እያልን በሰይጣን አሰራር ተከፋፈልን፡፡ ይህ ለአስተዳደር እንዲመች ተብሎ
የተከፋፈለው ከኢትዮጵያውነታችን ሊለየን አይገባም፡፡ አንድ ሁኑ ልዩነታችሁን ደግሞ ውበታችሁ ነውና አክብሩት፣ ጊዜያችሁን በትክክል
ተጠቀሙበት፤ በአልባሌ ቦታ እና በማይረቡ ነገሮች አትጨርሱ፡፡ ልጆቼ ከእእምሮ ባርነት የአካል ባርነት ይሻላልና ራሳችሁን ጠብቁ፡፡››
ብለው ሕዝቡም እየተገረመ አሸናፊን ‹‹ፈጣሪ እንኳን ማረህ! እንዲህ ዓይነት ሰይጣንም አለ እንዴ? ምን ዓይነት ዘመን ውስጥ ነው
ያለን? ሰይጣን ዓለምን የሚገዛበት ዘመን! ለካ የዘመኑ ሕጻናት፣ ልጆች ባጠቃላይ የሰው ጠባይ ክፉ የሆነው ለዚህ ነው እንዴ? ለካ
ወደው አይደለም ምን ያድርጉ የሚነዳቸው ሰይጣን ነው፡፡ጉድ ነው፣ ኧረ ፈጣሪ ያውጣን›› እያሉ ወደየማረፊያቸው ተበተኑ፡፡ አሸናፊም
በሆነው ነገር እጅግ ተደንቆ የደስታ እንባ እያነባ ወደ ተንቀሳቃሽ ድንኳኑ ነጻነትም ወደ ራሷ ድንኳን አመሩ፡፡ እኔም ቀኑ መሽቶ
ስለ ነበር በንጋታው ወደ ቤቴ ለመሄድ በሸራ ወደ ተሰራች ዳስ አመራው፡፡
2009 ዓ.ም
i have learning a lot of things from this story thanks regassa
ReplyDeleteThe Best 777 Casino Drive, Las Vegas, NV | MapYRO
ReplyDeleteThe BEST 777 하남 출장안마 CASINO 천안 출장안마 DR, Las Vegas, 영주 출장마사지 NV 89109. 계룡 출장마사지 Use map to find the best 777 Casino 평택 출장샵 Drive in Las Vegas, NV.