አስታውሳለሁ ብዙም ያልቆየ ነበር ባደኩበት ብዙ ብሔር ብሔረሰብ ያለበት እንዲሁም ክርስቲያን (ኦርቶዶክስ) እና እስልምና
ተከባብሮ የሚኖርባት ነበረች የትውልድ አካባቢዬ፡፡ ሁሉም በፍቅር ነበር በሀዘን ጊዜም ይሁን በደስታ ጊዜ ሁሉም እግዚአብሔርን የሚፈራ
ነበር፡፡ ክፋት ማሰብ የለም ወይ አብሮ መኖር! ሃይማኖታችን የተለያየ ቢሆንም ፍቅሩ ነበር፡፡ አንድ የትልቅ እድር አባል ነበርን
ሁላችንም ማለቴ ከሙስሊሞች ጋር ክርስቲያን ሲሞት ይቀብራሉ ሙስሊም ሲሞቱ ሄደን እንቀብራለን ነገር ግን ያ ዛሬ የለም ለምን ይሆን?
አስቡበት፡፡ይህን ያነሳሁት አሁን በሀራችን እየሆነ ወዳለው የዝናም አደጋ ለመምጣት ነው፡፡ የሆነው ከእግዚአብሔር እንደሆነ አይደለም
አኛ አእምሮ ያለን ሰዎች ሌሎች ፍጥረታትም ያውቃሉ፡፡ በታሪክ እንደምናውቀው ህዝበ እስራኤል እግዚአብሔርን በበደሉ ጊዜ መቅሰፍት
ያመጣባቸው ነበር ሲመለሱ ግን ይቅር ይላቸውና በበረከት ይጎበኛቸው ነበር፡፡ በሀገራችን ቢሆንስ በረከት አልነበረም ወይ? ወቅቱን
የጠበቀ እንደሚዘንብስ በእድሜያችን አላየንም ወይ? ዛሬስ ያ ዬት ሄደ?ሰሞኑን በድርቅ ምክንያት ብዙ ወገኖች፣እንሰሳት አጥተናል፤
እያጣንም ነው ዛሬ ደግሞ በተለየ መልኩ በጎርፍ የብዙ ሰው፣ሀብት ንብረት፣እንሰሳት፣ሊማት እየጠፋ ነው ለምን ይሆን?ሳይንሱ የሚለውን
ይላል፣የአየር መዛባት ነው፡፡ ይበለው፡፡ ለመሆኑ ለሰው ወሳኝ የሆኑ ነገሮች በሰው እጅ እንዳልገቡ እናውቃለን? ለምሳሌ አየር፣ዝናም፣ውኃ፣ነፋስ፣የፀሐይ
ብርሃን እና ሙቀት፣ወዘተ:: እነዚህ በሙሉ ላይ የሰው ልጅ ስልጣን የለውም ሁሉም በእግዚብሔር እና ከእግዚአብሔር ብቻ ናቸው፡፡
በሰው እጅ ቢሆኑ ኖሮማ የሰው ልጅ ለአንድ ደቂቃ እንካን ባልተረፈ ነበር፡፡እግዚአብሔርም ይህንን አውቆ በሰው እጅ እንዲገቡ አላደረገም፡፡
እሱ በፈቀደ ጊዜ ብቻ ያደርጋቸዋል፤ለመዓትም ለመህረትም ይጠቀምባችሃል ይሆናሉም አንድም ቀን ከተሰጣቸው ትእዛዝ ዝንፍ ብለው አያውቁም፡፡
ሰውስ?በዘመናችን እግዚአብሔርን መፍራት ይኖር ይሆን? ከመከፋፈል ውጪ ተባብሮ ማደግን፣ ሀገርን ማሳደግ፣በፍቅር መኖር፣ለሀገር መቆም
አለን? እውነት ዛሬ ለሀገር የሚቆም ሰው ይኖር ይሆን? ሙስና ለምን በዛ? መተማመኑስ ለምን ጠፋ? መለያየት ለምን ሰፈነ?ነው፡፡እዚህ
ላይ መጋቤ ሐዲስ እሴቱ የተናገሩት ነበር ስለ አሁኑ ሰው ‹‹እግዚአብሔር ጦርነት አያምጣና ዛሬ ጦርነት ቢሆን ዘራፍ ብሎ የሚነሳ
ሰው ያለ አይመስለኝም›› እንዲሁም አክለው ‹‹ዛሬ ኢትዮጵያ ቲሸጥ ቢባል ስንት ታወጣለች ብሎ ያስባል እንጂ ለምን ትሸጣለች ብሎ
አያስብም›› ብለዋል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ስለ
ሌለ ምክንያቱም ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲ ይባረካል›› መዝ. 128፡4 ይላል፡፡ በረከት ደግሞ የሰማይ እና
የምድር ነው፡፡ ዝናም በረከት ነው፣ሰላም በረከት ነው፣ፍቅር በረካት ነው... እግዚአብሔርን ካልፈራን ግን ለበረከት የተፈጠሩ ለጥፋት
ይታዘዙብናል ልክ እንደ ኖኅ ዘመን ውኃ፡፡አንድ ታሪክ ነው የሚነግራችሁ የዛሬ 15 ዓመት ያኔ መጀመሪያ ላይ የጠቀስካቸው በእምነት
የሚለያዩ ሰዎች በፍቅር በሚኖሩበት ጊዜ በአንድ ወቅት ዝናም ጠፋ ድርቅ ሆነ ይገርማል ሁሉም በሃይማኖት በብሔር ሳይለያይ ቤተክርስቲያን
ተሰባሰቡ (ሁሉም የአንድ እድር አባል ስለ ነበሩ - ቅድስት ማርያም እድር) ወደ ፈጣሪያቸው ለመኑ፡፡ ማታ ወደ ቤታቸው ሲመጡ የፈለጉት
ዝናም በሚፈልጉት ጊዜ በሚፈልጉት መጠን ዘነመላቸው፡፡ ዛሬስ እውነት ይህ አለ? በዚህ ሁኔታ እያሉ ነበር በሰው አእምሮ ፍልስፍና
ገባ ይህም በዓላትን መሻር፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ ‹‹አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው፡፡ ኑ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር
እንሻር አሉ›› መዝ. 74፡8 የኛዎቹም ማለት ጀመሩ፡፡ በፊት ቅዳሜ እና አሁድ፣ የእመቤታችን ዕለት፣የቅዱስ ሚካኤል ቀን እና የበዓለ
ወልድ በትክክል ያከብሩ ነበርና፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን በቅዳሜ እና እሁድ ማረስ፣ማጨድ፣መቆፈር ጀመሩ የተስማሙበትን አፈረሱ ከእድሩም
ሙስሊሞች ተለዩ ክርስቲያኑም የእድር ዕለት ዳቦ እና ጠላ ለመጠጣት ይሄዳል እንጂ ቀኑን የእሜታችንን አያከብርም፡፡ ከዚህ ቀኖች
ውጪ ባሉ ቀናት በመጠጥ ቤቱ እየዞረ፣እየተደባደቡ መገዳደል በዛ፣ሰው ሰውን ገድሎ የማያውቅባት ሀገር በየቀኑ፣በየሳምንቱ መሬት የሰውን
ደም መጠጣት ጀመረች፤የሰው ደም መጠጣት ስትጀምር ዝናም ተለያት፣በረከት ተለያት፣ጊዜን ያልጠበቀ ዝናም ያስቸግራት ጀመር፣ያልታሰበ
ድርቅ ይመታት ጀመር፣ገበሬው በሰራው ስራ መተማመኑ ጠፋ፣ከእግዚአብሔር ይልቅ ሳይንስ ላይ መደገፍ ጀመረ - የሚለውን ሞከረ ግን
በመቅሰፍት ቀን አላዳነውም፡፡ እግዚአብሔር ‹‹ያለኔ ምንም ልታደረጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል››
ዮሐ. 15፡5 ይል የለም ወይ?ዛሬስ ምክንያቱስ ምን ይሆን እንደዚህ የሆነው? ሰሞኑን ስለ ድርቅ ስናወራ ዛሬ ደግሞ በወላይታ የመሬት
ናዳ፣በባሌ እና በሌሎች ያልተጠበቀ ጎርፍ መከሰቱ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር እንመለስ፡፡ በክህደት መንገድ ያለን ወደ እምነት፣ለሱስ
የተገዛን ከባርነት እንውጣ፣ ዘረኝነት በሽታ የተያዝን እንታከም ያን ጊዜ ምህራት፣ቸርነት፣ሰላም፣ፍቅር፣በረከት ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል ‹‹ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤እግዚአብሔርም ከዘላለም ወደ ዘላለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ
በሳጣችሁ ምድር ተቀመጡ›› ት.ኤር. 25፡5፡፡ እኛም ወደ አባቶቻችን መንገድ እንመለስ፡፡
No comments:
Post a Comment