በእንተ ርእስየ

Friday, May 6, 2016

ማን ይሆን ትክክለኛው?

…በወሰነው ውሳኔ የሚጠቀም ካለ፣የሚተርፍ ሕይወት ካለ፣የሚድን ካለ፣የማይጠፋ ካለ እና የኛን ውሳኔ ሰው እና ዓለም ሳትሆን ሰማያዊያኑና ፈጣሪ የሚወደው ከሆነ ያሰብኩት ሀሳብ፣የወሰንኩት ውሳኔ ትክክል ነው ብሎ ማመን/ማሰብ እችላለው፡፡ያሰብኩት ሀሳብ የእግዚአብሔር ሀሳብ መሆኑን ለማወቅ ሕሊናዬ ካልተበላሸ በቀር ፈጣሪ የሚወደውን ይነግረኛል፡፡ ይህን ለማድረግ ያሰብኩት ሀሳብ ስጋዊ ነው ወይስ መንፈሳዊ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ስጋዊ ከሆነ ከዚህ ዓለም ነው፣ከሰይጣን ነው… መንፈሳዊ፤ነፍሳዊ ከሆነ ግን እሱስ የእግዚአብሔር ነው፡፡ ከውሳኔ በፊት መጀመሪያ ሕሊናን ማጽዳት ይቀድማል፡፡ መቅደም ያለበትን እናስቀድም ብዙ ያላስቀደምናቸው ነገሮች አሉና፡፡ በዚህ ዘመን ሰው አውቃለሁ፣የኔ ብቻ ከማለት ውጪ ያንተ ያንቺ ይብስ ማለትን ትቶታል ያን ጊዜ ትክክል መስሎ የሚታየው እሱ ያሰበው እሱ የወሰነው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን እንደዚያ ነው ወይ?

No comments:

Post a Comment