በእንተ ርእስየ

Wednesday, April 27, 2016

Mystery of apple/ የአፕል ምስጢሩ


ለመሆኑ አፕል / ከምፓኒ የ‹‹አፕልን›› ‹‹Apple›› ምልክት ለምን እንደተጠቀመው ያውቃሉ?
apple and its mystery









ምስጢሩን በቅርብ ይጠብቁ ፡፡ ሀሳብዎትን ያካፍሉ፡፡ 
 Apple Inc. Exposed

 

Saturday, April 23, 2016

መቅደም ያለበት ይቅደም

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቤተክርስቲያናችንን ከዘመኑ መናፍቃን ይበልጥ ለመታደግ መጀመሪያ እኛ ራሳችን ፍቅር ይኑረን፣ አንድ እንሁን ዘረኝነትን እናጥፋ፣ በክርስቶስ እንጂ በዘር (?)፣በጎጥ፣በወንዝ፣በብሔር፣በgg፣ ወዘተ አንድ አንሁን፡፡ ሃይማኖት ከዚህ ሁሉ በላይ ነውና፡፡ አባቶቻችን አንድ ሁኑ ይሉናል ራሳቸው መች አንድ ሆኑና፡፡ ወይም እንዴት አንድ መሆን እንዳለብን ግን አይነግሩንም (መጋቤ ሐዲስ እሼቱ)፡፡ የሃይማኖትን ትምህርት፤ አብነቱን፣ሌላውንም ትምህርት፣የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በልማድ እንጂ እውነት በእምነት ሲያደርጉ አናይም (ይህ ሲባል ሁሉም ሰው ማለት አይደለም)፣ የገባቸውማ አሉ አግዚአብሔር የባረካቸው ለቅድስና ያጫቸው ልክ እንደ ቅዱሳኑ ከዚህ ዓለም መከፋፈል የተለዩ ሁሉንም ሰው እኩል የሚወዱ ክርስቶስ ለእንድ ብሔር ሳይሆን ለዓለም ሁሉ እንደ ሞተ የገባቸው፡፡ ክርስቶስ የመሰረታት ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ለዓለም ሁሉ፣ለሁሉም በሔር ብሔረሰብ፤ለተቀበሉት ሁሉ እንጂ ለተወሰኑ ህዝቦች እንዳልሆነች በእምነተ እናስተውላለን፡፡ ባይሆንማ ኖሮ ጌታችን ‹‹የዓለምን ሐጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ›› ባልተባለ ነበር፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችንን ለጠላት አሳልፈን እንዳንሰጣት መጀመሪያ እኛው ራሳችን አንድ እንሁን፣የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስ፣ እኛ ባለን ሳይሆን ህዝቡ ባለው ነገር እንድረስለት ያን ጊዜ ይሰማል፣ይረዳል፣ይገበዋል አሁን ለምሳሌ ሐዋርያት በዘመናቸው የgg ችግር እንከን አላጋጠማቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱም ህዝቡ በሚሰማ ልሳን ይሰሙ ነበርና፡፡ ዛሬስ የኔን ካልሰማ እያልን አይደለም እንዴ?ይህ ማለት ያን ጊዜ ለሐዋርያት ልሳንን የገለጠ መንፈስ ቅዱስ ስህተት ነው አኛ ደግሞ ትክክል ነን ማለት እነደሆነ ግን አስተውለናል?ካልሆነማ የኛን ነገር አንጻበረቅን እንጂ መቼ የእግዚአብሔር ቃል አዳረስን፤አስተማርንና፡፡ እንዲህ ካልሆን ሊቃውንትም ሁኑ አባቶች ካህንም ይሁን ዲያቆን የወንጌል መምህርም ቢሆን ሁሉም በእግዚአብሔር ዘንድ እኩል መሆኑን ካላመነ፣ ክርስቶስ ለሁሉም እንደሞተ ካልተረዳ ለሆዱ ያደረ እንጂ ለክርስቶስ አይደለምና ቤተክስቲያንን ለጠላት አሳልፎ ይሰጣታል፡፡ በዉጪ ሀገር ቤተመጻሕፍት የሚገኙ የቤተክስቲያናቸን ቅዱሳት መጻሕፍት እውነት በውጭ ሀገር ሌቦች ብቻ ነው ወይ የተዘረፉት? የኛዎቹስ ለገንዘብ ለሆዳቸው ያደሩ አልሳተፉም ወይ? እሱን እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ በሃይማኖት ውስጥ ሆነን ዘረኛ፣ብሔርተኛ፣ጎጠኛ፣ጠባቦች፣የኔ ብቻ፣አኔ ብቻ ወዘተ ማለት የድንቁርና ምልክት ነው (ዲ/ን ሙሉጌታ:- የማኅበረ ቅዱሳን የቀድሞ ጸሐፊ)፡፡ በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ፈጽሞ የእግዚአብሔርን መንግስት ፈጽሞ ሊወርሱ አይችሉም (ገላ. 5) ለሌሎች ግን እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችንን ለመታደግ፣ ሁሉም እንድድን ዘረኝነት ከቤተክርስቲያናችን ይጥፋ፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ እኛው ራሳችን እንስተካከል፣አስተሳሰባችን ይለወጥ ሌላው በእግዚአብሔር ይቀላል ይቻላል፡፡ በ2ጢሞ.3፡1-10 ላይ ከተጠቀሱ የመጨረሻው ዘመን የሰው ጠባይ፤ሰዎች እንለይ፡፡

ታዲያ የክርስትና ድንበሩ ምኑ ጋር ነው? እኛ ዛሬ በማይረባ አእምሮ እየተመራን ክርስትናን አልገደብናትም ወይ::