በእንተ ርእስየ

Wednesday, October 25, 2017

ሕይወተ ወራዙት ክፍል 1/17-በአማርኛ

ክፍል አንድ
ምዕራፍ አንድ
መግቢያ
ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
ወጣትነት የተለያዩ የስጋ ፍላጎቶች ስሜታዊነት የሚያይሉበት በመሆኑ ልዩ የሆነ ጥበቃ የሚያስፈልገው የእድሜ ክልል ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል ቅዱስ ጴጥሮስን ‹‹ጠቦቴቼን ጠብቅ›› ብሎ አደራ የሰጠው ወጣቶች ነጻ ፈቃዳችንን ተጠቅመን በኃጢአት እንዳንወድቅ የሚጠብቀን እረኛ ስለሚያስፈልገን ነው፡፡ ወጣቶች ክፉ የሆኑ የስጋ ፍትወታት (ፍላጎቶች) ስለሚያይሉብን ለአያሌ ኀጢኣቶች የምንጋለጠው በዚህ ወቅት ነው፡፡ በዚህ የእሳትነት ዘመናችን ለማኅበራዊውም ሆነ ለመንፈሳዊ ሕግ ሁል ጊዜ እንጣላለን፡፡ የምንጣላውም ከሕጉ ወጣ ብለን በምንሰራው ስራ ነው፡፡
ክፉ የሆነ የወጣትነት ምኞት ዝም ብለው ከተከተሉት በኀጢአት ባህር ያሰጥማል፡፡ ንስሀ ካልገቡም ለሁለተኛ ሞት ያደርሳል፡፡ (ራዕ. 20፡14)፡፡ እኛ ወጣቶች በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ለመኖር የግድ ከኃጢኣት መለየት እና ከበደል መራቅ ይኖርብናል፡፡ ለዚህም ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግስትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ የወሀትን፣ መፍራት እና ራስን መግዛት ይጠበቅብናል፡፡ (ገላ. 5፡22) ይህ የሚሆነው ክፉ ከሆነ የጎልማሳነት ምኞት በመሸሽ የጭንቀት ቀንም ሳይመጣ በጉብዝናችን ወራት እግዚአብሔርን ስናስብ ነው፡፡ መክ. 12፡2፣ 2ጢሞ. 2፡12፡፡
ይህ እንዴት ይቻላል ብሉ በማር. 9፡23 ‹‹ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል›› ቆላ. 4፡13 ‹‹ኃይልን በሚሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ›› መልሳችን ነው፡፡
ሙሉ ሰው የሚባለው ወጣት ነው፡፡ ወጣት ማለት ሎጋ፣ ሸበላ፣ ልጅ እግር፣ መዘዞ፣ ቀንበጥ ማለት ሲሆን በተጨማሪም ጎልማሳ ጎበዝ፣ ለዘር የበቃ፣ አፍላ ማለት ነው፡፡ ግእዙ ወጣት ማለት ‹‹ወሬዛ›› ለብዙ ደግሞ ወራዙት ይሆናል፡፡ ሙሉ ሰው የሚባለው ንዋያት የተሟሉለት ማለትም ሕዋሳት ተደራጅተውለት እንደ ልቡ ማሰብ፣ መንቀሳቀስ እና መናገር የሚችል ሰው ነው፡፡ ሙሉ ሰው ኃላፊነት መውሰድ ይችላል፣ ስለ ራሱ መግለጥ ይቻለዋል፡፡
ዘመነ ወርዛዌ
የወጣትነት ዘመንን በቁጥር ሰፍሮ ከዚህ እስከዚህ ያለው ነው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ መጻሕፍት አሀዛዊ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እና ምሳሌአያዊ አስተምህሮ ወጣትነት የሚባለው ከ20-40 ዓመት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከነፋስ፣ ከእሳት፣ ከውኃ ከአፈር እና አምስተኛው ከነፍስ ነው፡፡ እነዚህ አራቱ ባሕሪያት በሰው ሕይወት ውስጥ ይንጸባራቃሉ፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ አራቱም ወደነበሩበት ይመለሳሉ፡፡ ያን ጊዜ ሥጋ ይበሰብሳል፡፡ ብትንሣኤ ዘጉባኤ ደግሞ አራቱም ባሕሪያት ከነፍስ ጋር እንደገና ተዋሕደው ይነሳሉ፡፡ ሰው በነዚህ አራቱ ባሕርያት እራሱን እንዲገዛ ተደርጎ ነው የተፈጠረው፡፡ አራቱ ባሕርያት የሚጣሉ ናቸው፤ የሚታረቁም ናቸው፡፡ ለምሳሌ እሳት ስያይል በውሃ እንድናበርድ፣ ነፋስ ስያይል በመሬትነታችን እንድንገታ ነው፡፡ እንዲህ ካልሆነ በሰው ሕይወት እንሰሳዊነት ጠባይ ብቻ ይንጸባረቃል፡፡ በውስጣችን ስለመኖራቸውም መገለጫዎቹ እንደሚከተሉ ናቸው፡፡
ነፋስ፡- ሰው በመተንፈሱ ከነፋስ መፈጠሩ ይታወቃል
እሳት፡- በጤናማ ሕይወት የሚታየው ቋሚ የሰውነት ሙቀት መኖሩ ከእሳት መፈጠሩ ይታወቃል
 ውኃ፡-ከሰውነት ብዙ ውኃ መኖሩ፣ መለስለሱ ከውኃ መፈጠሩ በዚህ ይታወቃል
መሬት፡- ሰው በሕይወት ሳለ መጠንከሩ፣ ሲሞት መበስበሱ፣ የመሬት ጠባያትን መያዙ ከመሬት እንደተፈጠረ ይገልጻል (ዘፍ. 3፡19)
ማቴ. 15፡20
‹‹የዘመኖቻችን ዕድሜ ሰባ ዓመት ቢበዛም ሰማንያ ዓመት ነው፡፡›› (መዝ. 89፡10) ይህን ዕድሜ አራቱ ባሕርያት እኩል ይካፈሉታል፡፡ አራቱም በአንድነት ቢዘልቁም በተለየ መልኩ ጎልተው የሚታዩት ሃያ ሃያ ዘመን አላቸው፡፡
ከ0-20 ዓመት የነፋስ ባሕርይ- ዘመነ ነፋስ ይባላል፡፡ ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳል፡፡ ሕጻናት እንደመሰላቸው ሽው ሽው ይላሉ፡፡ ዮሐ. 3፡8፡፡ ነፋስ ምንም እንደማያሳይ ሁሉ በምግበ ነፋስ ያሉ ሕጻናትም ብዙ የሚያስተውሉት ነገር የለም፡፡ ዐለዋቂነት ያጠቃቸዋል፡፡ የያዙትን ውድ ነገር (ሃይማኖት፣ ድንግልና...) ዋጋ ለሌለው ብልጭልጭ፣ ገንዘብ ወዘተ ነገር ለመለወጥ በቀላሉ ይታለላሉ፡፡ ኤፌ. 4፡14፡፡ እስኪ ቆም ብለን የኛን ሕይወት እናስብ በዚህ እድሜ ያጣናቸው ነገሮች የሉም ወይ?
20-40 ዓመት የእሳት ባሕርይ- ዘመነ እሳት ይባላል፡፡ ወጣት የሚያሰኘው ይህ ነው፡፡ ‹‹ፋይር ኤጅ›› የሚባለው ከቤተ ክርስቲያን የተገኘ ነው፡፡ እሳት ብሩህ እንደሆነ ሁሉ ወጣቶችም ክፉ እና ደጉን የሚያስለይ የእውቀት ብርሃን አላቸው፡፡ ሆኖም እሳት ያገኘውን ልብላ (ላቃጥል) እንደሚል ወጣቶችም ሁሉ የሚያምራቸው እና ትምክህተኞች ናቸው፡፡
40-60 ዓመት የውኃ ባሕርይ- ዘመነ ማይ ይባላል፡፡ ብሩህነት ቀዝቃዛነት የውኃ ጠባይ እንደሆነ ሁሉ በዚህ እድሜ የደረሱ ሰዎችም በነገሮች ሁሉ ረጋ ማለትን ማስተዋልን ይጀምራሉ፤ የወጣትነት ዘመናቸውን ወደ ኋላ እየተመለሱ በግርምት ይመለከቱታል፡፡
60-80 ዓመት የመሬት ባሕርይ ዘመነ አፈር ይባላል፡፡ ደረቅነት፣ ጨለማነት፣ ቀዝቃዛነት የመሬት ጠባይ እንደሆነ ሁሉ በዚህ እድሜ የደረሱ ሰዎች ለነገሮች ግትርነት፣ የሚያማርሩ፣ የሚያዝኑ፣ ለትንሽ ነገር የሚከፉ፣ ሞት ሞት የሚሸታቸው፣ ፍቅረ ንዋይን አጥብቀው የሚወዱ ወዘተ ናቸው፡፡ እድሜያቸው ለዚህ የደረሱ ሰዎች ለሀብት ሲጨነቁ አላያችሁም? አቅም ስለሌላቸው ገንዘብን ለሁሉ ነገራቸው መሠረት አድርገው ስለሚያስቡ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሰው የእድሜ ክልል ዓመቱን ጠብቆ ይከሰታል ማለት አይደለም ነገር ግን በመካከላቸው ጦርነት ስላለ አንዱ ያለ ጊዜው ሊከሰት ሌላው ደግሞ ሊዘገይ ይችላል፡፡ የወጣትነት እድሜ ከ20 ዓመት ቀድሞ ሊጀምርም ይችላል ልክ እንደዛሬው ዘመን፡፡ ዘመኑ ክፉ ነውና እናስተውል፡፡
ስለ አራቱ ባሕርያት መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ ስነ ፍጥረት እና ሌሎችንም ያንብቡ፡፡
ዖዝያን የአስራ ስድስት ዓመት ሆኖ ሳለ ጎልማሳ (ወጣት) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ (2ዜና. 26፡1)፡፡ ጎልማሳነት ደግሞ እስከ አርባ ዓመት ሊቆይ እንደሚችል ‹‹ኢዮሳፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበር፡፡ (2ዜና. 20፡31)
ወጣቶች በመልካም አኗኗር ከኖሩ የ‹‹ልጅ አዋቂ›› ይባላሉ፡፡ ከፈቀዱ አረጋዊ መሆንና አረጋዊ ከደረሰበት ፀጋ እና ክብር መድረስ ይችላሉ፡፡ የወጣት ሥራ የሚሰሩ ሽማግሌዎች እንዳሉ ሁሉ የሽማግሌ ሥራ የሚሰሩ ወጣቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ወጣት ሆነው የሚያስታርቁ... (ተግ.ዘዮሐ.አፈ. 7)
አረጋዊ ዮሴፍ ሽማግሌ ሲሆን ድንግል ማርያምን ለመጠበቅ ተመርጧል፡፡ ወጣቱ ወንጌላዊ ዮሐንስም በቅቶ ስለተገኘ ለአረጋዊ ዮሴፍ የተሰጠችውን ድንግል ማርያምን ከመስቀሉ ሥር በመገኘት በአደራ ተቀብሏል፡፡ ይህ የሆነው ፀጋን ለመቀበል በቅቶ መገኘት እንጂ እድሜ ወሳኝ አለመሆኑን ያስረዳል፡፡ ጸጋ እግዚአብሔር በእድሜ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ድንግል ማርያም ትንሽ ብላቴና ሆና ሳለች ጸጋን የተመላች ተባለች፡፡ ወጣቶች ከአረጋዊያን ሊበልጡ ይችላሉ፡፡ ‹‹መከበር በዘመን ብዛት አይደለም›› ጠቢቢ ሶሎሞን ‹‹ጥበብን የሚያውቃት እድሜ የጠገበ አይደለም›› ይላልና፡፡
ጥሩ ወጣት መሆን ያስፈልጋል፤ ካልሆነም ብዙ ነገር ይታጣል፡፡ ለሌሎች ምሳሌ መሆን ይሳነናል፡፡ ሽማግሌው እንደ ወጣት ሊሆን ቢል ከቅጣት እንደማያመልጥ ሁሉ ወጣቶችም ሕግ ሲያፈርሱ የሚነቀፉበት ብዙ ነገር አለ፡፡ ሽማግሌ በፍቅረ ንዋይ ቢፈተን እርጅናው ስለመጣበት ደክሞ የሚረዳው ይሻልና ገንዘብ ካለኝ በገንዘቤ እጦራለሁ ብሎ ነው ይባላል፡፡ ወጣቶች ደግሞ ወጥተው ወርደው እራሳቸውን መርዳት ስለሚችሉ በፍቅረ ንዋይ ቢያዙ ይነቀፋሉ፡፡ ዛሬ ስራ ትተው የሚሰርቁ፣ የሚዘርፉ፣ ሙስናው ወዘተ ምንጩ ይህ እኮ ነው፡፡በዚህም ብቻ ሳይሆን ንጽሕናቸውን ባለመጠበቃቸው ፣ በሰካራምነታቸው፣ በስንፍናቸው እና በመሳሰሉት መጥፎ ስራቸው ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ንጽሕናን ጠብቀን ለመኖር አንችልም እንዳይሉ ንጽሕናን ለመጠበቅ ያላቸውን አጋዥ ኃይል መመልከት በተገባቸው ነበር፡፡ ወጣቶች አረጋዊያን የሌላቸው ኃይለ ስጋ ስላላቸው ፍትወትን ለማሸነፍ ሲሉ መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድ እና መጻሕፍትን መመልከት ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመጠየቅም የተለያዩ ቅዱሳን ቦታዎችን በመሄድ በረከት ማግኘት ይችላሉ ምክንያቱም ከቅዱሳን ቦታዎች የቅዱሳንን በረከት በቀላሉ ማግኘት ይቻላልና፡፡
ይቀጥላል

ክፍል አንድ
ምዕራፍ አንድ
መግቢያ
ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
ወጣትነት የተለያዩ የስጋ ፍላጎቶች ስሜታዊነት የሚያይሉበት በመሆኑ ልዩ የሆነ ጥበቃ የሚያስፈልገው የእድሜ ክልል ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል ቅዱስ ጴጥሮስን ‹‹ጠቦቴቼን ጠብቅ›› ብሎ አደራ የሰጠው ወጣቶች ነጻ ፈቃዳችንን ተጠቅመን በኃጢአት እንዳንወድቅ የሚጠብቀን እረኛ ስለሚያስፈልገን ነው፡፡ ወጣቶች ክፉ የሆኑ የስጋ ፍትወታት (ፍላጎቶች) ስለሚያይሉብን ለአያሌ ኀጢኣቶች የምንጋለጠው በዚህ ወቅት ነው፡፡ በዚህ የእሳትነት ዘመናችን ለማኅበራዊውም ሆነ ለመንፈሳዊ ሕግ ሁል ጊዜ እንጣላለን፡፡ የምንጣላውም ከሕጉ ወጣ ብለን በምንሰራው ስራ ነው፡፡
ክፉ የሆነ የወጣትነት ምኞት ዝም ብለው ከተከተሉት በኀጢአት ባህር ያሰጥማል፡፡ ንስሀ ካልገቡም ለሁለተኛ ሞት ያደርሳል፡፡ (ራዕ. 20፡14)፡፡ እኛ ወጣቶች በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ለመኖር የግድ ከኃጢኣት መለየት እና ከበደል መራቅ ይኖርብናል፡፡ ለዚህም ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግስትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ የወሀትን፣ መፍራት እና ራስን መግዛት ይጠበቅብናል፡፡ (ገላ. 5፡22) ይህ የሚሆነው ክፉ ከሆነ የጎልማሳነት ምኞት በመሸሽ የጭንቀት ቀንም ሳይመጣ በጉብዝናችን ወራት እግዚአብሔርን ስናስብ ነው፡፡ መክ. 12፡2፣ 2ጢሞ. 2፡12፡፡
ይህ እንዴት ይቻላል ብሉ በማር. 9፡23 ‹‹ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል›› ቆላ. 4፡13 ‹‹ኃይልን በሚሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ›› መልሳችን ነው፡፡
ሙሉ ሰው የሚባለው ወጣት ነው፡፡ ወጣት ማለት ሎጋ፣ ሸበላ፣ ልጅ እግር፣ መዘዞ፣ ቀንበጥ ማለት ሲሆን በተጨማሪም ጎልማሳ ጎበዝ፣ ለዘር የበቃ፣ አፍላ ማለት ነው፡፡ ግእዙ ወጣት ማለት ‹‹ወሬዛ›› ለብዙ ደግሞ ወራዙት ይሆናል፡፡ ሙሉ ሰው የሚባለው ንዋያት የተሟሉለት ማለትም ሕዋሳት ተደራጅተውለት እንደ ልቡ ማሰብ፣ መንቀሳቀስ እና መናገር የሚችል ሰው ነው፡፡ ሙሉ ሰው ኃላፊነት መውሰድ ይችላል፣ ስለ ራሱ መግለጥ ይቻለዋል፡፡
ዘመነ ወርዛዌ
የወጣትነት ዘመንን በቁጥር ሰፍሮ ከዚህ እስከዚህ ያለው ነው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ መጻሕፍት አሀዛዊ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እና ምሳሌአያዊ አስተምህሮ ወጣትነት የሚባለው ከ20-40 ዓመት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከነፋስ፣ ከእሳት፣ ከውኃ ከአፈር እና አምስተኛው ከነፍስ ነው፡፡ እነዚህ አራቱ ባሕሪያት በሰው ሕይወት ውስጥ ይንጸባራቃሉ፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ አራቱም ወደነበሩበት ይመለሳሉ፡፡ ያን ጊዜ ሥጋ ይበሰብሳል፡፡ ብትንሣኤ ዘጉባኤ ደግሞ አራቱም ባሕሪያት ከነፍስ ጋር እንደገና ተዋሕደው ይነሳሉ፡፡ ሰው በነዚህ አራቱ ባሕርያት እራሱን እንዲገዛ ተደርጎ ነው የተፈጠረው፡፡ አራቱ ባሕርያት የሚጣሉ ናቸው፤ የሚታረቁም ናቸው፡፡ ለምሳሌ እሳት ስያይል በውሃ እንድናበርድ፣ ነፋስ ስያይል በመሬትነታችን እንድንገታ ነው፡፡ እንዲህ ካልሆነ በሰው ሕይወት እንሰሳዊነት ጠባይ ብቻ ይንጸባረቃል፡፡ በውስጣችን ስለመኖራቸውም መገለጫዎቹ እንደሚከተሉ ናቸው፡፡
v  ነፋስ፡- ሰው በመተንፈሱ ከነፋስ መፈጠሩ ይታወቃል
v  እሳት፡- በጤናማ ሕይወት የሚታየው ቋሚ የሰውነት ሙቀት መኖሩ ከእሳት መፈጠሩ ይታወቃል
v  ውኃ፡-ከሰውነት ብዙ ውኃ መኖሩ፣ መለስለሱ ከውኃ መፈጠሩ በዚህ ይታወቃል
v  መሬት፡- ሰው በሕይወት ሳለ መጠንከሩ፣ ሲሞት መበስበሱ፣ የመሬት ጠባያትን መያዙ ከመሬት እንደተፈጠረ ይገልጻል (ዘፍ. 3፡19)
ማቴ. 15፡20
‹‹የዘመኖቻችን ዕድሜ ሰባ ዓመት ቢበዛም ሰማንያ ዓመት ነው፡፡›› (መዝ. 89፡10) ይህን ዕድሜ አራቱ ባሕርያት እኩል ይካፈሉታል፡፡ አራቱም በአንድነት ቢዘልቁም በተለየ መልኩ ጎልተው የሚታዩት ሃያ ሃያ ዘመን አላቸው፡፡
ከ0-20 ዓመት የነፋስ ባሕርይ- ዘመነ ነፋስ ይባላል፡፡ ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳል፡፡ ሕጻናት እንደመሰላቸው ሽው ሽው ይላሉ፡፡ ዮሐ. 3፡8፡፡ ነፋስ ምንም እንደማያሳይ ሁሉ በምግበ ነፋስ ያሉ ሕጻናትም ብዙ የሚያስተውሉት ነገር የለም፡፡ ዐለዋቂነት ያጠቃቸዋል፡፡ የያዙትን ውድ ነገር (ሃይማኖት፣ ድንግልና...) ዋጋ ለሌለው ብልጭልጭ፣ ገንዘብ ወዘተ ነገር ለመለወጥ በቀላሉ ይታለላሉ፡፡ ኤፌ. 4፡14፡፡ እስኪ ቆም ብለን የኛን ሕይወት እናስብ በዚህ እድሜ ያጣናቸው ነገሮች የሉም ወይ?
20-40 ዓመት የእሳት ባሕርይ- ዘመነ እሳት ይባላል፡፡ ወጣት የሚያሰኘው ይህ ነው፡፡ ‹‹ፋይር ኤጅ›› የሚባለው ከቤተ ክርስቲያን የተገኘ ነው፡፡ እሳት ብሩህ እንደሆነ ሁሉ ወጣቶችም ክፉ እና ደጉን የሚያስለይ የእውቀት ብርሃን አላቸው፡፡ ሆኖም እሳት ያገኘውን ልብላ (ላቃጥል) እንደሚል ወጣቶችም ሁሉ የሚያምራቸው እና ትምክህተኞች ናቸው፡፡
40-60 ዓመት የውኃ ባሕርይ- ዘመነ ማይ ይባላል፡፡ ብሩህነት ቀዝቃዛነት የውኃ ጠባይ እንደሆነ ሁሉ በዚህ እድሜ የደረሱ ሰዎችም በነገሮች ሁሉ ረጋ ማለትን ማስተዋልን ይጀምራሉ፤ የወጣትነት ዘመናቸውን ወደ ኋላ እየተመለሱ በግርምት ይመለከቱታል፡፡
60-80 ዓመት የመሬት ባሕርይ ዘመነ አፈር ይባላል፡፡ ደረቅነት፣ ጨለማነት፣ ቀዝቃዛነት የመሬት ጠባይ እንደሆነ ሁሉ በዚህ እድሜ የደረሱ ሰዎች ለነገሮች ግትርነት፣ የሚያማርሩ፣ የሚያዝኑ፣ ለትንሽ ነገር የሚከፉ፣ ሞት ሞት የሚሸታቸው፣ ፍቅረ ንዋይን አጥብቀው የሚወዱ ወዘተ ናቸው፡፡ እድሜያቸው ለዚህ የደረሱ ሰዎች ለሀብት ሲጨነቁ አላያችሁም? አቅም ስለሌላቸው ገንዘብን ለሁሉ ነገራቸው መሠረት አድርገው ስለሚያስቡ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሰው የእድሜ ክልል ዓመቱን ጠብቆ ይከሰታል ማለት አይደለም ነገር ግን በመካከላቸው ጦርነት ስላለ አንዱ ያለ ጊዜው ሊከሰት ሌላው ደግሞ ሊዘገይ ይችላል፡፡ የወጣትነት እድሜ ከ20 ዓመት ቀድሞ ሊጀምርም ይችላል ልክ እንደዛሬው ዘመን፡፡ ዘመኑ ክፉ ነውና እናስተውል፡፡
ስለ አራቱ ባሕርያት መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ ስነ ፍጥረት እና ሌሎችንም ያንብቡ፡፡
ዖዝያን የአስራ ስድስት ዓመት ሆኖ ሳለ ጎልማሳ (ወጣት) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ (2ዜና. 26፡1)፡፡ ጎልማሳነት ደግሞ እስከ አርባ ዓመት ሊቆይ እንደሚችል ‹‹ኢዮሳፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበር፡፡ (2ዜና. 20፡31)
ወጣቶች በመልካም አኗኗር ከኖሩ የ‹‹ልጅ አዋቂ›› ይባላሉ፡፡ ከፈቀዱ አረጋዊ መሆንና አረጋዊ ከደረሰበት ፀጋ እና ክብር መድረስ ይችላሉ፡፡ የወጣት ሥራ የሚሰሩ ሽማግሌዎች እንዳሉ ሁሉ የሽማግሌ ሥራ የሚሰሩ ወጣቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ወጣት ሆነው የሚያስታርቁ... (ተግ.ዘዮሐ.አፈ. 7)
አረጋዊ ዮሴፍ ሽማግሌ ሲሆን ድንግል ማርያምን ለመጠበቅ ተመርጧል፡፡ ወጣቱ ወንጌላዊ ዮሐንስም በቅቶ ስለተገኘ ለአረጋዊ ዮሴፍ የተሰጠችውን ድንግል ማርያምን ከመስቀሉ ሥር በመገኘት በአደራ ተቀብሏል፡፡ ይህ የሆነው ፀጋን ለመቀበል በቅቶ መገኘት እንጂ እድሜ ወሳኝ አለመሆኑን ያስረዳል፡፡ ጸጋ እግዚአብሔር በእድሜ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ድንግል ማርያም ትንሽ ብላቴና ሆና ሳለች ጸጋን የተመላች ተባለች፡፡ ወጣቶች ከአረጋዊያን ሊበልጡ ይችላሉ፡፡ ‹‹መከበር በዘመን ብዛት አይደለም›› ጠቢቢ ሶሎሞን ‹‹ጥበብን የሚያውቃት እድሜ የጠገበ አይደለም›› ይላልና፡፡
ጥሩ ወጣት መሆን ያስፈልጋል፤ ካልሆነም ብዙ ነገር ይታጣል፡፡ ለሌሎች ምሳሌ መሆን ይሳነናል፡፡ ሽማግሌው እንደ ወጣት ሊሆን ቢል ከቅጣት እንደማያመልጥ ሁሉ ወጣቶችም ሕግ ሲያፈርሱ የሚነቀፉበት ብዙ ነገር አለ፡፡ ሽማግሌ በፍቅረ ንዋይ ቢፈተን እርጅናው ስለመጣበት ደክሞ የሚረዳው ይሻልና ገንዘብ ካለኝ በገንዘቤ እጦራለሁ ብሎ ነው ይባላል፡፡ ወጣቶች ደግሞ ወጥተው ወርደው እራሳቸውን መርዳት ስለሚችሉ በፍቅረ ንዋይ ቢያዙ ይነቀፋሉ፡፡ ዛሬ ስራ ትተው የሚሰርቁ፣ የሚዘርፉ፣ ሙስናው ወዘተ ምንጩ ይህ እኮ ነው፡፡በዚህም ብቻ ሳይሆን ንጽሕናቸውን ባለመጠበቃቸው ፣ በሰካራምነታቸው፣ በስንፍናቸው እና በመሳሰሉት መጥፎ ስራቸው ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ንጽሕናን ጠብቀን ለመኖር አንችልም እንዳይሉ ንጽሕናን ለመጠበቅ ያላቸውን አጋዥ ኃይል መመልከት በተገባቸው ነበር፡፡ ወጣቶች አረጋዊያን የሌላቸው ኃይለ ስጋ ስላላቸው ፍትወትን ለማሸነፍ ሲሉ መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድ እና መጻሕፍትን መመልከት ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመጠየቅም የተለያዩ ቅዱሳን ቦታዎችን በመሄድ በረከት ማግኘት ይችላሉ ምክንያቱም ከቅዱሳን ቦታዎች የቅዱሳንን በረከት በቀላሉ ማግኘት ይቻላልና፡፡
ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment