ክፍል ስድስት
ምዕራፍ ሦስት
ምትረተ እስኪት- አባለ
ዘርዕ መቁረጥ
በሀገራችን
ሌላውን መስለብ እንደ ባህል የሚነገርላቸው አንዳንድ ጎሳዎች እና ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡ ዳዊትም ሜልኮልን ለማግባት የመቶ ፍልስጤማውያን
ሸለፈት ሰልቦ ማምጣት ነበረበት፡፡ 1ሳሙ. 18፡25-27
ዛሬም
በፍትወት ከመቃጠልና ከመበሳጨት የተነሣ ብዙ መንፈሳዊያንና ዓለማውያን ብልቶቻቸውን በመቁረጥ አደጋ ላይ እየወደቁ ይገኛሉ፡፡ ድንግልናቸው
እንዲጠበቅ ደግሞ የልጃ ገረዶችን ብልት የሚተለትሉና የሚሰፉ ብዙ ጎሳዎች በሀገራችን አሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም የጽድቅ መንገድ
አይደለም ከባድ ስሕተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ጭምር ነው፡፡ ፍትወት ከልክ በላይ ሆኖ ቢያስቸግርህ አካልን በመቁረጥ ወይም ለማምለጥ
አታስብ፡፡ ይህ የሰይጣን ወጥመድ ነው፡፡ መፍትሔው ማግባት ነው፡፡ 1ቆሮ. 7፡9፡፡ ብልት መቁረጥ ማለት ሰርቆ የተያዘ ሰው ከሚደርስበት
ድብደባ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ይህ ራስ አጥፊነት፣ ቀጪነት ነው፡፡
ሰው
በዝሙት ጊዜ የሚበድለው በአባለ ዘሩ ብቻ ሳይሆን በልቡናውና በሕሊናውም ጭምር ነው፡፡ ሰይጣን ብልት ካስቆረጠ በኋላ እንድንጸጸት
በማድረግ ራሳችንን እንድናጠፋ ያነሳሳል፡፡ ልክ እንደ ይሁዳ፡፡ ማቴ. 27፡3-5 ሐዋ. 1፡16-20፡፡ በፍትወት መቃጠል የሚመነጨው
ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ነው፡፡ ምትረተ እስኪት ስሜታዊነትን፣ ሽንፈትን፣ ስንፍናን፣ ስልቹነትን፣ ታካችንትን፣ አርቆ አለማሰብን ያመለክታል፡፡
በጾም፣ በጸሎት እና በስግደት ማሸነፍ እያለ በቅጽበት ለመገላገል ማሰብ ነውና፡፡
በመጻሕፍትም
ቢሆኑ ‹‹ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን ጀንደረባ ያደረጉ›› ማለቱ ስለ ብልት መቁረጥ አይደለም፡፡ ‹‹ኀፍረተ አካሉን የቆረጠ
ሰው ካህን ቢሆን ይሻር›› ‹‹ብልቱ የተቆረጠ ሰው ወደ እግዚአብሐየር ጉባኤ አይግባ›› ዘዳ. 23፡1፡፡ ነገር ግን ያለውድ፣ በግድ፣
በጦርነትና በልዩ ልዩ ደዌ ምክንያት አባለ ዘራቸው የተቆረጠ ሰዎች ከላይ የተጠቀሰው እገዳ አይመለከታቸውም፡፡
በመጽሐፈ
መነኮሳት ‹‹አካል ብልት የጎደላቸውን ሰዎች አታዋርዳቸው›› (ማር.ይስ. አን. 2 ምዕ. 13) በመጽሐፍ ቅዱስም አንድ ሰው የሰውን
ብልት ቢይዝ እጁ ይቆረጥ ማለቱ ጥንቃቄ ሊደረግለት እንደሚገባ እና ክብሩ ከእጅ የሚበልጥ መሆኑን ያሳያል፡፡
በተለያዩ
ጊዜያት እጃቸውን (አባ አትናቴዎስ)፣ ዐይኑን በወስፌ እንዳወጣ (ስምዖን ጫማ ሰፊ)፣ እግሩን በእሳት እንዳቃጠለ (አባ መርትያኖስ)
ብልትን መቁረጥ ከእነዚህ ይለያል፡፡ ምክንያቱም በዋናነት የተሰናከሉት እነርሱ ራሳቸው አልነበሩም ይልቅ ሌሎች አካላቸውን በማየት
ስለተሰናከሉ መሰናክል የሆነውን አካላቸውን በማስወገድ ለሌሎች ያላቸውን ፍቅርና ኀዘኔታ ሕዋሳታቸውን እስከ ማስወገድ ደርሰው አሳዩ፡፡
እነዚህ አካላት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ኀፍረተ ስጋ ግን ከጥንትም ቢሆን በልብስ ይሸፈናል፡፡ ኀፍረተ አካል ከሌሎች ሕዋሳት በላይ ሊታይ
ይገባዋል፡፡ ሌሎች ንዑሳን አካላት ናቸው፡፡ ምክንያቱም ኀፍረተ ስጋ ሕይወት መተላለፊያ ነው፡፡ 1ቆሮ. 12፡23 ‹‹በምናፍርባቸው
ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል፡፡›› ተብሏልና፡፡
ከሰይጣነ
ዝሙት ፈተና የተነሣ እንኳን አባለ ዘርን መቁረጥ ይቅርና ‹‹ምነው ከማህፀን ጃንደረባ ሆኜ በተወለድሁ ኖሮ›› በማለት መመኘትም
ስሕተት ነው፡፡ ለዚህም ‹‹ዝሙትን እንድትፈጽም ሰይጣን ባስጨነቀህ ጊዜ አባለ ዘርዕን አትቁረጥ፡ ከእናትህም ሆድ ጀምሮ ጃንደረባ
መሆንን አትፈልግ፡፡›› (ፊልክ.ተስእ.186) እንዲሁም በፈቃዱ ራሱን የሰለበ ለሦስት ዓመት ከቤተ ክርቲያን ይሰደድ፡፡ (ፍት.ነገ.አን.24)
ይቀጥላል

No comments:
Post a Comment